በሰሜን ሸዋ ዞን በስድስት ቀናት ብቻ ከ250 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ

በሰሜን ሸዋ ዞን በአምስት ወረዳዎች ከጥር 13 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት በዘለቀው የፀጥታ ችግር ከ250 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የዞኑ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታዉቋል ።

በዞኑ በሸዋሮቢት ፣ በአጣየ ፣ በቆዎጅ ፣ በኤፍራታ እና በአንፆኪያና ገምዛ ወረዳዎች በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከተፈናቀሉ ከ250 ሺ በላይ ሰዎች መካከል ከ74 ሺህ በላይ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ናቸው ተብሏል ። ከነዚህም መካከል 5 ሺ 719 የሚሆኑት እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች መሆናቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሮምነሽ ጋሻውጠና ተናግረዋል ።

በተጨማሪ በሰላም መደፍረሱ ከ180 በላይ ህፃናት ወላጆቻቸዉን እንዳጡ ተገልጿል ። የችግሩ አስከፊነት በተለይም በህፃናት ፣ በአካል ጉዳተኞች ፣ በነፍሰጡሮች ፣ በሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም በአረጋውያን የከፋ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ርሃብ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል ። አብዛኞቹ ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ፣ የተዘረፈባቸው መሆናቸው ተገልጿል ። ለተፈናቀሉ ሰዎች አስቸኮይ ሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልግ በመሆኑ ከመንግስት እና ከረድኤት ድርጅቶች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል ። በአጣየ እና ኤፍራታ በህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀዉ የሸኔ ቡድን ለዘጠነኛ ጊዜ ጥቃት ከሁለት ሳምንት በፊት መክፈቱ ሲል ብስራት ሬዲዬ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe