በሱዳን በተለያዩ ግዛቶች ህዝባዊ አመፅ ቀጥሏል፤ የሰሜን ኮርዶፋን ግዛትም አስቸኳይ ጊዜ አውጇል

የሱዳን ሽግግር መንግስት በአዲስ ካቢኔ ቢዋቀርም በተለያዩ ግዛቶች የተቀሰቀሰው አመፅ ግን ሊቆም አልቻለም።
ሰሜን ዳርፋር ኤልፋሻር #el fashar ዛሬ በቀጠለው ተቃውሞ በርካታ የመንግስት ተቋማት ወድመዋል። በዚያው በዳርፋር #ነያላ ከተማ ለተቃውሞ የወጣው ህዝብ ከፀጥታ ሃይሎች መሳሪያን በመንጠቅ ወደ ዘረፋ አምርቷል ። የገበያ ሱቆች፣ መኖሪያ ቤቶች እና የመንግስት ተቋማትን ሲዘርፋ ዉለዋል። በምስሉ እንደሚታየው ፀጥታ ለማስከበር የመጡ የፖሊስ ሰራዊት ተሽከርካሪዎችን ጭምር አቃጥለዋል።
ኤል ጀኒና በሚሰኝ አካባቢ ከሶስት ሳምንት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን አልበረደም።ተመድ እንዳስታወቀው እስካሁን 163ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 130 ሺህ ያህሉ ተሰደዋል።
በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት የሚካሄደው ተቃውሞ ከቁጥጥሩ ውጭ በመሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፏል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ካሊድ ሙስጠፋ እንዳሉት እየጨመረ የመጣውን የህይወት ማጣት እና የንብረት ውድመት ለመቆጣጠር ሲባል የተላለፈ ውሳኔ ነው።
በሪቨር ናይል ግዛት የባቡር ድርጅት ሰራተኞች ትላንት የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሏል። ሃገራዊ የኢኮኖሚ ጫናውን መቋቋም አልቻልንም ያሉት ሰራተኞቹ የደሞዝ ጭማሪ እስካልተደረግላቸው በስራ ማቆም አድማው እንደሚቀጥሉ አል ሃዳት አል ሱዳን ሚዲያ ዘግቧል።
መግባባት የተሳነው የሱዳን ሽግግር መንግስት 26 ሚኒስትሮች ያሉትን አዲስ ካቢኔ ትላንት ምሽት በጠ/ሚር አብደላ ሃምዶክ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
በሰላም ሙሉጌታ ተፃፈ
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe