በሶደሬ ሪዞርት ሕገ ወጥ ስልጠና ሲወስዱ የሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ሶደሬ ሪዞርት ውስጥ ሕገ ወጥ ስልጠና ሲወስዱ ከነበሩ 68 ሰዎች ውስጥ 53 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዳይሬክተር ኮማንደር ጸጋዬ ቶላ፣ እነዚህ ግለሰቦች “ፎሌ የጥበቃ፣ ጽዳትና ስልጠና” የተባለ ተቋም ሲያሰለጥናቸው ነበር ብለዋል፡፡

“ሶደሬ ሪዞርት ስልጠና የሚሰጥበት ቦታ አይደለም፣ ሲሰጥ የነበረው ስልጠናም ሕገ ወጥ ነበር” ብለዋል ኮማንደሩ፡፡

ኮማንደር ጸጋዬ፣ ለጥበቃ ስራ ከሚውሉ የጦር መሳሪያዎች ውጪ ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ተከማችተው መገኘታቸውን ገልጸው፣ የቡድን ጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ 29 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ፎሌ የጥበቃ፣ ጽዳትና ስልጠና ተቋም እነዚህን ግለሰቦች ለጥበቃ ስራ እንደሚያሰለጥናቸው የገለጸ ቢሆንም፣ እንደዚህ ዓይነት ስልጠና ሲሰጥ በፖሊስ መምሪያ እውቅና መሆን ነበረበት፤ በስልጠና ላይ የነበሩ ሰዎች ማንነትና እንዴት ለስልጠናው እንደተመረጡ መገለጽ ነበረበት ብለዋል ኮማንደር ጸጋዬ፡፡

ኮማንደር ጸጋዬ ስልጠናው በሌሊት ሲሰጥ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ሕጋዊ ፍቃድና እንዳለውና እንደሌለው፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች እየተጣሩ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር ጸጋዬ፣ ጉዳዩን መከታተል ሲገባቸው ክትትል ያላደረጉ የመንግስት አካላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

SourceOBN~ EBC
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe