በሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው የቤት ማፈረስ እና በግዳጅ ማስነሳት ዘመቻ አድሎአዊ እርምጃ ስለመኖሩ ኢሰመኮ አመለከተ

በሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው የቤት ማፈረስ እና በግዳጅ ማስነሳት ዘመቻ አድሎአዊ እርምጃ ስለመኖሩ የኢሰመኮ የክትትል ሪፖርት አመልክቷል።

” መንግሥት የሚወስዳቸው ማናችውም እርምጃዎች ከአድሎ የጸዱ መሆን እንደሚገባቸው በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች እና በሀገር አቀፍ ሕጎች እውቅና ከተሰጠው የሰብአዊ መብቶች መርሆች መካከል አንዱ ነው ” ያለው ኮሚሽኑ ክትትልና ምርመራ ባደረገባቸው አንዳንድ ቦታዎች ላይ አድሏዊ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንዳሉ ለመመልከት መቻሉን አሳውቋል።

ለአብነት በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ቄስ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተያይዘው ከተሠሩ ቤቶች ውስጥ ሁለት ቤቶችን በማስቀረት ሌሎች ቤቶች እንዲፈርሱ ተደርገዋል።

ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች አድሎው ብሔር ተኮር እንደሆነ እምነት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን የመንግሥት ኃላፊዎች ግን ይህ እንዳልሆነ አስረድተዋል ሲል ኮሚሽኑ በላከልን የክትትል ሪፖርት ገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe