በቀን ስምንት ሰዓት ብቻ ሰርተን ያሰብነውን ልናሳካ አንችልም

 “በቀን ስምንት ሰዓት ብቻ በመስራት የትም ልንደርስና ያሰብነውን ልናሳካ ስለማንችል ሁላችንም ተጨማሪ ጊዜ ሰጥተን ልንሰራ ይገባል” ሲል አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ ተናገረ።
አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በተለይ ለኢዜአ እንደገለፀው፤ ኢትዮጵያ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግስት መመስረት መቻሏ ጫና ለመፍጠር ለሚሹ አገሮች ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው።
“አዲሱ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትጋት በመስራት የተጣለበትን አገራዊ ሃላፊነት በብቃትና በላቀ አፈፃፀም መወጣት አለበት” ብሏል።
“የኢትዮጵያን የልማት እቅድ ለማሳካት በቀን ስምንት ሰዓት ብቻ በመስራት የትም ልንደርስና ያሰብነውን ልናሳካ ስለማንችል ሁላችንም ተጨማሪ ጊዜ ሰጥተን ልንሰራ ይገባል” ብሏል ሻለቃ ሃይሌ።
የመንግስት አካላት ከህዝቡ ጋር ተባብረው ለኢትዮጵያ እድገት መስራትና ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝቧል።
“ኢትዮጵያዊያን የአገራችንን ህልውና ማስጠበቅ ቀዳሚ ስራችን ሊሆን ይገባዋል” በማለት ገልጾ፤ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ፍላጎት ያላቸው አገራት ቀዳሚ አጀንዳ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ እና ኢትዮጰያ በተፈጥሮ ሃብቷ እንዳትለማና ከድህነት እንዳትወጣ በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ለመያዝ መሆኑን ጠቅሷል።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን ሴራ በቅጡ በመረዳት ለአገሩ ህልውና የዘወትር ዘብ ሊሆን እንደሚገባ ገልጿል።
“ኢትዮጵያ ጀምራለች’’ ያለው አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ፤ ኢትዮጵያ እየተጋፈጠችው ያለው ችግር እንደሚፈታ ያለውን ጽኑ እምነት ተናግሯል።
የትኛውም አካል በኢትዮጵያ ላይ ጊዜያዊ ችግር ሊፈጥር ይችል የሆናል ፈፅሞ ሊያፈርሳት አይችልም ነው ያለው።
ኢትዮጵያዊያን ከአዲሱ የመንግስት አስተዳደር ጎን በመቆም የአገራችንን ልማት ማስቀጠል፣ ህልውናዋን ማስጠበቅና ሉአላዊነቷን ማስከበር አለብን ብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe