በቀድሞ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ የሕይወት ታሪክ ላይ ትኩረት አደርጎ የተጻፈው መጽሐፍ ተመረቀ

ቀድሞ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ የሕይወት ታሪክ ላይ ትኩረት አደርጎ የተጻፈው “ከተማ ይፍሩ የሰላም ዕድገትና የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ” የተሰኘው መጽሐፍ ተመረቀ።
መጽሐፉ በልጃቸው መኮንን ከተማ ይፍሩ ተፅፎ ለንባብ የበቃ ሲሆን በእንግሊዘኛና በአማርኛ ቋንቋዎች የታተመ ነው።
የመጽሐፉ ፀሐፊ መኮንን ከተማ እንደተናገሩት መጽሃፉ በቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት ምስረታና የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ይዳስሳል።
በተለይም ሥመ-ጥሩ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ በያኔው አፍሪካ አንድነት ድርጅት ምሥረታ የነበራቸው ትልቅ ሚናም በመጽሃፉ ትኩረት እንደተደረገበት ጠቁመዋል።
ያም ብቻ ሳይሆን ከተማ ይፍሩ የፓናፍሪካኒዝም እሳቤ እንዲያብብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ግንኙነት ዙሪያ ያበረከቱት ሚናም መካተቱን ተናግረዋል።
መጻሐፉ መዘጋጀቱ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ ለአገራቸው በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያበረከቱትን አስተዋጽዖ ለትውልድ ለማስተዋወቅ ያግዛል ብለዋል።
በተለያዩ ምዕራፎች የተከፋፈለው ይኽው መጽሃፍ 280 ገፆች አሉት።
ለበርካታ ጊዜያት በተለያዩ መድረኮች ላይ ኢትዮጵያን የወከሉት ከተማ ይፍሩ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች ማገልገላቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe