በቅርቡ 11 ኛ ክልል ሆኖ የተደራጀው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከባድ የበጀት ችግር እንደገጠመው ተሰማ፤

ከለውጡ በኋላ ከደቡብ ክልል ተገንጥሎ ራሱን ችሎ  እንደ አዲስ የተደራጀው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ከባድ የበጀት እጥረት እንዳጋጠው አስታወቀ፤

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ለኢቢሲ እንደተናገሩት ክልሉ ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተገንጥሎ እንደ አዲስ ሲደራጅ አብዛኛውን በጀቱን ከቀድሞው ክልል ጋር ያለ የንብረት ክፍፍል ላይ ማተኮሩንና በዚህም ሳቢያ አስተዳደራዊ ወጪዎች መናሩን ተናግረዋል፤

ክልሉ ይህንን የበጀት ጉድለት ለማሟላት በነገው ዕለት በሸራተን አዲስ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን የገለፁጽ ዶ/ር ነጋሽ በክልሉ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያሉ በመሆኑ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱና ክልሉን እንዲደግፉ ጠይቀዋል፤

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የበጀት እጥረት ላጋጠመው ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተመለክቷል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe