በበይነ-መረብ(online) እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው የግል ተቋማት ቁጥር 5  ብቻ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ  ስራ ላይ በዋለው በበይነ-መረብ ትምህርት የእውቅና አሰጣጥ መመሪያ  መሰረት ፈቃድ በበይነ-መረብ(online) እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው የግል ተቋማት ቁጥር 5 መድረሱን የከፍተኛ ትህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ኤጀንሲው ለ4 ተቋማት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን አሁን ላይ ለሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ኦፍ አድሚኒስትሬሽን የትምህርት መስክ በድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር በበይነ-መረብ የትምህርት አሰጣጥ ተማሪ ተቀብሎ እንዲያስተምር መፍቀዱን አሳውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ  በበይነ-መረብ(በኦንላይን) ሞዳሊቲ የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ  መርሃ-ግብር እንዲያስተምሩ በኤጀንሲው የተፈቀደላቸው 5 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

1) ኢቲ ኦንላይን ኮሌጅ

2) ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ

3) ኤስቲ አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ

4) ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ እና

5) ላይፍ ማፕ ኮሌጅ ናቸው፡፡

ከተጠቀሱት 5 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ ሲሆኑ፤ ሌሎች በበይነ-መረብ (በኦንላይን) ትምህርት  የእውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው  ያላቸው በማስመሰል  በተለያዩ የኢንተርኔት አውታሮች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁ ህገ-ወጥ አካላት መኖራቸው ታውቆ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሁሉም ህብረተሰብ አካላት ጥንቃቄ  እንዲያደርጉ ኤጀንሲው በጥብቅ አሳስቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe