በባሕር ዳር ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ የሰው ሕይወት ማለፉን፤ በአካል እና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱ ፖሊስ ገለጸ

በባሕር ዳር ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

 (አብመድ) አደጋው መንስኤ እና የደረሰው ጉዳት ላይ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

እንደ ፖሊስ መረጃ ቃጠሎው የተከሰተው ትናንት ማታ 5፡00 አካባቢ ነው፡፡ በዚህም የሰው ሕይወት ማለፉን፤ በአካል እና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ስለአደጋው መንስኤ እና ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጉዳዩን እያጣራ መሆኑንም ነው መምሪያው የገለጸው፡፡

ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ መምሪያው ዝርዝር መረጃውን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ ከወራት በፊት በደረሰ የእሳት አደጋ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸው እና የከተማ አስተዳደሩና የከተማዋ ነዋሪዎች ተጎጂዎችን የማቋቋም ሥራ እያከናወኑ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe