በባንግላዲሽ በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼኪ ሃሲና ለአምስተኛ ዙር አሸነፉ

ሼክ ሃሲና የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚንስትር ሆና ለመቀጠል ለአምስተኛ የስልጣን ዘመን ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል።ውጤቱ በበህዳር ወር መጀመሪያ ላይ ይፋ ይደረግ የነበረ ቢሆንም የባንግላዴሽ ዋንኛ  የተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫው ላይ ባነሱት ቅሬታ የተነሳ ውጤቱ ሳይገለፅ ቆይቷል። በምርጫውም ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ይልቅ ነፃ እጩዎች በድምሩ 63 መቀመጫዎችን አግኝተዋል።

የገዢው የሀሲና አዋሚ ከፍተኛው 222 የምክር ቤት መቀመጫዎችን በማግኘት ስልጣኑን አራዝሟል። የአሁኑ የተቃዋሚ ፓርቱ የሆነው ጃቲያ ፓርቲ ከ300 የፓርላማ መቀመጫዎች ማግኘት የቻለው 11ዱን ብቻ መሆኑን የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል። የምዕራባውያን መንግስታት ነፃ፣ ፍትሃዊ እና አሳታፊ የህዝብ አስተያየት እንዲኖር በሃሲና መንግስት ላይ ጫና ካደረጉ በኋላ ብቸኛው ጥርጣሬ የመራጮች ተሳትፎ ነበር ሲባል ቆይቷል።
የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርቲያቸው ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የፓርላማ መቀመጫ  ማሸነፋቸውን ተከትሎ የዓለማችን ረጅም ዓመታትን ያስተዳደሩ ሴት ርዕሰ መስተዳድር የሚለውን ማዕረጋቸውን ይዘው ይቀጥላሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሯ አመራር በድህነት ውስጥ የነበረችውን ሀገር የኢኮኖሚ እድገቷን በማፋጠን ረገድ በበላይነት የመሩ ቢሆንም መንግስታቸው ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና በተቃዋሚዎች ላይ ርህራሄ በሌለው መልኩ እርምጃ ይወስዳል በሚል ይከሰሳል።

ምርጫው የተካሄደው ከ300 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ በ299ኙ ነው። በአንድ የፓርላማ መቀመጫ ላይ ክፍተት የመጣው በምርጫው ህጉ ላይ በተደነገገው መሰረት አንድ ገለልተኛ እጩ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ ምርጫው እንዲራዘም ተደርጓል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe