በቤት ውስጥ በተከሰተ የእሳት አደጋ የ6 ልጆች እናት ህይወት አለፈ፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ጀረምስ ቀበሌ በተለምዶ መንደር ሁለት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ ላይ በቤት ውስጥ በተከሰት የእሳት አደጋ የ6 ልጆች እናት ህይወት አልፏል ፡፡ የእሳት አደጋውን አያይዘው መረጃውን በስልክ ያደረሱን የጀረምስ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ አላቸው መሸሻ እንደተናገሩት የእሳት አደጋው የተከሰተው በቤት ውስጥ ምሽት ላይ ሲነድ በቆየ እሳት ነው ብለዋል ፡፡
በዚህ ቤት ውስጥ የተከሰተው እሳት ትናትና ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ ቤቱን ሲያቀጣጥል በተሰቡ በሙሉ ከወጡ በሗላ ሴትዬዋ እቤት የተቀመጠ ገንዘብ ለማውጣት ወደ ቤት ተመልሳ ገብታ እንደሆነና የአካባቢው ማህበረሰብም ሴትዬዋ እንደገባች ሳያይ ቤቱን ለማዳን ባደረገው ጥረት የቤቱን ግማሽ ማዳን ሲችሉ በተቃጠለው ቤት ውስጥ ግን የሴትዬዋ ህይወት አልፎ ተገኝቷል ፡፡
የእሳት አደጋ ከዚህ በፊትም በወረዳችን ሀብት ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ ሁሉም የአካባቢያችን ኗሪዎች በኩሽና /ማዕድ/ ቤት ውስጥ ምግብ ስናበስል ጥንቃቄ እንድናደርግና በመጨረሻም ማጥፋታችንን ልናረጋግጥ ይገባል ፡፡
መረጃው የደባይ ጠላት ግን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe