በቴሌ ብር በቀን አምስት ቢሊዮን ብር ዝውውር ይደረጋል ተባለ

በቴሌ ብር አማካኝነት አንድ ነጥብ ስድስት ትሪሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር ተደርጓል
የቴሌ ብር አገልግሎት ወደ ሥራ ከገባ ጊዜ ጀምሮ አንስቶ አንድ ነጥብ ስድስት ትሪሊዮን ብር ዝውውር መደረጉን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ። በቀን የአምስት ቢሊዮን ብር ዝውውር እንደሚደረግም አስታውቋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፤ የቴሌ ብር በዲጂታል አማራጭነት ወደ ሥራ ከገባ በኋላ የአንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ገንዘብ ዝውውር ተደርጓል።
25 ባንኮች ከቴሌ ብር ጋራ ገንዘብ ዝውውር በማድረግ በትስስር እየሰሩ ይገኛል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ በዚህም የየዕለት የገንዘብ ዝውውሩ ሲታይ በቀን አምስት ቢሊዮን ብር ዝውውር ይደረጋል ብለዋል።
በቀን ዝውውር ከሚደረገው የገንዘብ መጠን 19 በመቶ የሚሆነው ከሌሎች ባንኮች ወደ ቴሌ ብር የሚገባ ሲሆን፤ 21 በመቶ የሚሆነው ከቴሌ ብር ወደ ሌሎች ባንኮችና የዲጂታል ፋይናንሲንግ አማራጮች የሚዘዋወር መሆኑን አስረድተዋል።
ከአጠቃላዩ የገንዘብ ልውውጥ 42 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ በኢ-ብር ግብይት ላይ ይውላል ሲሉ ተናግረው፤ ይህም ኢኮኖሚን ከገንዘብ ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ ለመገንባት ያለው ሚና የጎላ መሆኑን.አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe