በትራፊክ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው ተሰማ

በከባድ የትራፊክ አደጋ ሳቢያ ከደርዘን በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል ተባለ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተሰማው፡፡

ከሟቾቹም ባለፈ በርካቶች ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡

በዚሁ የትራፊክ አደጋ ምክኒያት 19 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 13 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት መጋለጣቸው ተነግሯል፡፡

አደጋውን ያደረሰው ተሸከርካሪ ኤክስካቫተር የጫነ ተሳቢ ሲሆን ፌሬን መቆጣጠር ባለመቻሉ መንገድ ዳር የነበረን ሆቴል ጥሶ ገብቶ ነው የ19 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረገው፡፡

ተሸከርካሪው ወደ ከተማ ሲገባ የፌሬን ችግር እንደነበረበት ኬላ ላይ ለፍተሻ መቆም ባለመቻሉ ታውቆ እንደነበርም የግልገል በለስ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተናግረዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በአደጋው የተሰማውን የሀዘን መግለጫ አውጥቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe