በትግራይ ክልል ህብረተሰቡ እስከ መጋቢት 10 ባሉት ቀናት ውስጥ ብቻ አሮጌዉን ብር ሙሉ በሙሉ እንዲቀየር ማሳሰቢያ ተሰጠ

በትግራይ ክልል ህብረተሰቡ አሮጌዉን ብር ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 10 ባሉት ቀናት ውስጥ ብቻ በአዲሱ እንዲቀየር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አሳሰበ።

ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ ሀገሪቱ አሮጌዉን ብር በአዲስ የመቀየሩ ሥራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ባንኩ አስታውሷል፡፡

በክልሉ በነበረዉ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ሳቢያ ብር የመቀየሩ ሂደት ተስተጓጉሎ እንደነበር ያስታወሰ ሲሆን ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ከ100 ሺህ ብር በታች አሮጌ ብር ያላቸዉ እንዲቀይሩ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ተፈቅዶ እንደነበረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ላይ አመልክቷል።

እስካሁን ባለዉ በክልሉ ይቀየራል ተብሎ የሚታሰበዉ አሮጌ የገንዘብ መጠን በአብዛኛዉ የተቀየረ በመሆኑና የሚቀየረዉ አሮጌ ገንዘብ መጠንም በጣም ጥቂት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በክልሉ የተጀመረዉን ብር የመቀየር ሥራ ለማጠናቀቅ የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን  እንዲቀየር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉ ተጨማሪ ቀናት አሮጌዉ ብር ሙሉ በሙሉ እንዲቀየር ጥሪ ቀርቧል።

ይህ ማሳሰቢያ የመጨረሻ መሆኑ ታዉቆ የባንክ ቅርንጫፍ በተከፈተባቸዉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በመሄድ ይኸዉ ተግባራዊ እንዲደረግ፤ ባንኮችም በዚሁ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

Sourceፋና
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe