በትግራይ ክልል በተፈፀመ ጥቃት የቆሰሉት ተመራቂ ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል

በትግራይ ክልል ዓዲመስኖ በተባለው ቦታ ላይበታጣቂዎች  የቆሰሉ የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

የቆሰሉትና ከጥቃቱ አካላዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው ወደ አዲስ አበባ ከገቡት ሃያ ስምንቱ ተመራቂዎች ትላንት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲያርፉበት ካዘጋጀላቸው ሆቴል ድረስ በመሄድ አመሻሹ ላይ የቆሰሉትን ተማሪዎች የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደወሰዷቸው የሆስፒታሉ ክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት አሳውቀዋል።

ዶክተር ይርጉ ሶስቱ በጥይት አጥንታቸውን ስለተመቱ ተኝተው እየታከሙ ነው ብለዋል።

ቀሪ አምስት ቁስለኞች በተመላላሽ መታከም እንደሚችሉ ዶክተር ይርጉ ገ/ህይወት ገልፀዋል።

ቆስለው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ካሉ ተመራቂዎች መካከል ስድስቱ በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ፍንጣሪ ያገኛቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ተመራቂዎቹ እንደተናገሩት ያረፉበት “ካሌብ ሆቴል” ምግብ ሆስፒታል ድረስ እያመላለሰላቸው ነው፡፡ ተመራቂዎቹ ከደረሰባቸው ጥቃት ባሻገር ንብረታቸውን በመዘፈረፉ የካሌብ ሆቴል ሰራተኞች ገንዘብ አዋጥተው ቅያሪ ቲሸርት ገዝተው እንደሰጧቸው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe