ኮሚሽኑ የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በሰብአዊ መብቶች የሚመሩ መሆን አለባቸውም ብሏል።ቀደም ሲል በኢሰመኮ የቀረቡ፣ በተለይም በሲቪል ሰዎች ላይ ማንኛውም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲደረግ አጽንዖት የሚሰጡት ምክረ ሃሳቦችንና ጥሪዎችን በማስታወስ፣ በቀጣይ የሚደረጉ የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ተግባራት በፌዴራል መንግሥቱ ሰብአዊ መብቶችን የማክበርና የመጠበቅ ግዴታ የሚመራ እንዲሆን አሳስቧል።የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙና ተገቢው ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን የተቋረጡ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ ውሃና ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ አካላት አገልግሎት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ማሳሰቡን ኮሚሽኑ በላከው መግለጫ ገልጿል።
<በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ ተመረቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!>
እንዲሁም በግጭቱ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ሰዎች ወደ መደበኛ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እና የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙ የሚያስችል አስፈላጊ የሆነው የሎጂስቲክስና የሰብአዊ እርዳታ መሰረተ ልማት እንዲደራጅም ጠይቋል።ተጠያቂነትን ለማረጋገጥና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ያስከተለውን ሰብአዊ ቀውስ የሚመመረምር ገለልተኛና ግልጽ የሆነ አሰራር ከወዲሁ እንዲተገበር፣ ተዓማኒና አካታች የሆኑ የእርቅና የፍትሕ ሂደቶች በጊዜ ሊደራጁ ይገባልም ብሏል።በተጨማሪም ኢሰመኮ በትግራይ ተወላጆች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረገ መድሎዎና መገለል ስለመድረሱ የሚቀርቡለት ቅሬታዎች በከፍተኛ ደረጃ እያሳሰበውና እየተከታተለው መሆኑን ገልጿል።