በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን በተመለከተ ሁሉቱ ሚኒስትር መ/ቤቶች እርስ በእርሱ የሚጋጭ መግለጫ ሰጡ

በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከሉን አልሰማንም ያሉ ሰዎች ገዝተው እያመጡ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አለመከልከሉን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቀል፤

መስሪያ ቤታቸውም በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በተባለው አግባብ ብቻ እንደሚሰራ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ማንኛውም የቤት አውቶሞቢል የኤሌክትሪክ ካልሆነ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ መንግስት ቀደም ሲል ውሳኔ ማሳለፉን ሚኒስትሩ ዓለሙ አንስተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በዛሬው እለት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመስሪያ ቤታቸውን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ለከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት መሆኑን ሸገር ራዲዮ ዘግባል፡፡

ለተሽከርካሪዎች ነዳጅ የሚወጣው የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ መሆኑ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በስፋት መመረቱ እና ከነዳጅ ጋር ሲነፃፀር ርካሽ መሆኑ እንዲሁም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ደጋፊ መሆኗ በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ለመጣል ምክንያት ከሆኑት መካከል ይገኙበታል ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በአለም ላይ በስፋት እየተመረቱ መሆኑንን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በሀገር ውስጥም ለሀይል መሙያ (ቻርጅ ማድረጊያ) ቦታዎችን በቶሎ ማዳረስ ይቻላል ብለዋል፡፡

ማንኛውም የግል መገልገያ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የሚቻለው የኤሌክትሪክ ከሆነ ብቻ መሆኑንን ያሰመሩበት ሚኒስትር ዓለሙ ሰሞኑንን ይህን አልሰማንም በሚል በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ገዝተው ያመጡ መኖራቸውን አስድተዋል፡፡

በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አለመከልከሉን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ

በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አለመከልከሉን  የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊ ገለጹ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከትናንት በስቲያ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፓርላማው የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ አውቶሞቢሎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ውሳኔ መተላለፉን ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕግ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ እንዳደይገቡ በመከልከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ የሚፈቅድ ምንም ዓይነት መመሪያም ሆነ ውሳኔ የለም፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል እየተከናወነ ያለው ሥራ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማበረታታትና በነዳጅ የሚሠሩት ደግሞ በብዛት እንዳይገቡ ተስፋ ለማስቆረጥ፣ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ የተደነገገበት ሁኔታ መኖሩን አቶ ዋሲሁን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማገድ በዓለም የንግድ ድርጅት ሕግ መሠረት የማይቻል በመሆኑ፣ የአገሪቱን የቀረጥ ሥርዓት በመጠቀም ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቅሙትን ማበረታት፣ ጎጂ የሆኑትን ደግሞ እንዳይስፋፉ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe