በነጌታቸው አሠፋ መዝገብ ተከሰው የታሰሩ 22 ተከሳሾች በዋስትና እንዲፈቱ ወሰነ፤

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቀድሞው የደኅንነት ሹም ጌታቸው አሠፋ መዝገብ ተከሰው የታሰሩ 22 ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ወሰነ፤

አቃቤ ህግ ውሳኔውን ተቃውሞ ይግባኝ ሊጠይቅ መሆኑ ተሰምቷል፤

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት  ዛሬ በድምጽ ብልጫ የወሰነው  በቀድሞው የደኅንነት ሹም ጌታቸው አሠፋ መዝገብ ተከሰው ከ3 ዓመታት በፊት የታሰሩ 22 ተከሳሾች ላይ ሲሆን  እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ነው በድምጽ ብልጫ የወሰነው፤

 ሆኖም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ እንዲጣልባቸው አዟል። በዋስትና እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው መካከል፣ በብሄራዊ መረጃ እና ደኅንነት ባለሥልጣን የቀድሞው የሀገር ውስጥ ደኅንነት መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ዘሪሁን እና የጸረ-ሽብር ወንጀል መምሪያ የቀድሞው ሃላፊ ተስፋዬ ኡርጌ ይገኙበታል።

አቶ ያሬድ በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲከሰሱ  አቶ ተስፋዬ ለተለያዩ ግጭቶች ድጋፍ በመስጠት ወንጀል ክስ እንደተመሠረተባቸው ይታወሳል።

አቃቤ ህግ የዛሬውን ፍርድ ቤቱን የዋስትና ውሳኔ ተቃውሞ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለመጠየቅ መወሰኑ ሲሰማ ተከሳሾቹ በዘመነ ኢህአዴግ ለተፈፀሙ በርካታ የመብት ጥሰቶችና በሰብዓዊነት ላይ ለተፈፀሙ የጭካኔ ተግባራት ዋና ሀላፊ ናቸው በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ይታወሳል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe