በናይጄሪያ የዩንቨርሲቲ መምህራን የስራ ማቆም ዓድማ ሊያደርጉ ነው 

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ የዩንቨርሲቲ መምህራንን የሥራ ማቆም ዓድማ ሚኒስትሮቻቸው በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አዘዙ፡፡

ቡሀሪ የናይጄሪያ የትምህርት እና ሰራተኛ ሚኒስትሮች የተራዘመውን የዩንቨርሲቲ መምህራን የሥራ ማቆም ዓድማ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ማቋጫ እንዲያበጁለት አዘዋል፡፡
የአገሪቱ የዩንቨርሲቲዎች አካደሚክ ስታፍ ኅብረት(ኤኤስዩ) ዓባላቱ የካቲት ላይ በስራ ገበታቸው እንዳይገኙ ማዘዙን ተከትሎ እስካሁን መምህራኑ ወደ ዩንቨርሲቲያቸው አልተመለሱም፡፡
መንግስት ከአስርት ዓመታት በፊት የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ አላደረገም በሚል ነው ዓድማው ተጀመረው፡፡
ስምምነቱ ለዩንቨርሲቲ መምህራን የተሻለ ክፍያን የሚያበስር እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተለያዩ ግብዓቶች መሟላት እንዳለበት የሚደነግግ ነበር ፡፡
ማኅበሩም የወሰድንው እርምጃ ከተማሪዎች ጥቅም እና ፍላጎት አንጻር ነው የሚል ግንዛቤ አለው፡፡
የማኅበሩ ባለስልጣናት እና የናይጄሪያ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ መፍትሔ ለማምጣት ቢሰሩም አሁንም አልተሳካላቸውም ፡፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዩንቨርሲቲዎች አካዳሚክስ ስታፍ ኅብረት አፈንግጦ የወጣው የናይጄሪያ ዩንቨርሲቲ አካዳሚክስ ኮንግረስ በተራዘመው የስራ ማቆም ዓድማ ላይ የለሁበትም ዓይነት ሀሳቡን ከቀናት በፊት ገሀድ ማድረጉ የሚዘነጋ አይደለም ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe