ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለ መክሰሙን ይፋ ያደረገው ግዕዝ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ ድርጅቱን ከውድቀት ለመታደግ 12 አባላት ያሉት የሽምግልና ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ትልልቅ ስራ ፈጣሪዎች እጅ ለማዞር ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም በግለሰቦች መካከል ባለው አለመስማማት ወደ መክሰም አምርቷል ነው ያለው፡፡
እነዚህ የውስጥ እና የውጭ ድክመቶች ተቋሙ ላይ የእምነት ማጉደል እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ በዚህም በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲየጣ አድርጎታል ነው ያለው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ለውጥ ምክኒያት የምስረታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ እንዲከሽፍ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡
12 አባላት ያሉት የሽምግልና ኮሚቴ ተቋሙን ወደ ትልልቅ ስራ ፈጣሪዎች እጅ ለማዘዋወር ጥረት ሲደረግ ቢቆይም በአቶ አብርሃ ገብረአህዋድ የሚመሩ ሦስት ግለሰቦች አንፈርምም በማለታቸው ሳይሳካ መቅረቱንም ገልጻል፡፡
ባንኩ የምስረታ ሂደቱ በአግባቡ ባለመጠናቀቁ እና ወደ መፍረስ በማምራቱ ለባላክሲዎኖች የተዋጣውን ገንዘብ እንደሚመለስ ተናግሯል፡፡ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት አንድ ባንክ በምስረታ ሂደት ከአምስት ዓመት በላይ መቆት አይችልም፡፡ ግዕዝ ባንክ አክሲዮን መሸጥ ከጀመረ መጋቢት 7 አምስት ዓመት ሞልቶታል፡፡ በህጉ መሠረትም ባንኩ የባላክሲዎኖችን ገንዘብ መመለስ እንዳለበት ያስገድደዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ባንኮች የንግድ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ገንዘቡን ለባለአክሲዮኖች እንዲመልሱ ከብሔራዊ ባንክ ጋር መወያየቱንም ገልጻል፡፡//

