በአማራ ክልል በየ7ቀኑ ከመቶ በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ እየተጠቁ ነው ተባለ

በአማራ ክልል በየ7ቀኑ ከመቶ በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ እየተጠቁ ነው ተባለ፡፡

በ7 ወር ጊዜ ውስጥ ከ5ሺ በላይ ሰዎች በበሽታው ተጠቅተው ከ30 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን እንዳጡ ተሰምቷል፡፡

በክልሉ የእብድ ውሻ በሽታ ወይም ራቢስ ከሌላው ጊዜ በተለየ በአሁኑ ስዓት መጨመሩን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

ውሻን በመኖሪያ ቤት ውስጥ አስሮ አለመያዝ እና ክትባት አለማስከተብ ለበሽታው መስፋፋት ምክኒያት እንደሆኑም ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም በእብድ ውሻ የተነከሱ ሰዎችም ወደ ህምክና ተቋም የመሄድ ልምዳቸው ዝቅተኛ መሆኑ አባባሽ ነው ተብሏል፡፡ በአማራ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ከ5ሺ በላይ ሰዎች በበሽታው ተጠቅተዋል ከ32 በላይ የሚሆት ደግሞ ከበሽታው ጋር በተገናኘ መሞታቸውን ጤና ኢንስቲትዩቱ ይፋ አድርጓል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe