በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለኤፍ ቢ ሲ አስታውቋል፡፡

ዘንድሮ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ህዳር ወር ሊሰጥ የነበረው ክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ እንደነበር ተገልጿል።

በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በሰሜን ወሎ ዞን ዋግኸምራ፣ ሰሜን ጎንደር ፣ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ውስን አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነበር።

አሁን በክልሉ ሰላም በመፈጠሩ የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ከትናንት ጀምሮ እንደተከፈቱ ቢሮ ገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe