በአርባምንጭ ከአንድ ታካሚ ሆድ ውስጥ በርካታ ባዕድ ነገሮች በቀዶ ጥገና መውጣቸው ተሰማ

ከቀዶ ሕኪምና በኋላ ታካሚው በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛልም ነው የተባለው።

የህክምና ባለሙያዎች ታካሚው ባለፉት 4 ወራት ውስጥ በርካታ ቁሳቁሶች ሳይውጥ እንዳልቀረም ነው የጠቆሙት።

በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአንድ ታካሚ ሆድ ውስጥ በርካታ ባዕድ ነገሮች በቀዶ ጥገና መውጣቸው ተሰማ፡፡

በግለሰቡ ሆድ ውስጥ ተገኙ የተባሉት ባዕድ ነገሮች የተለያዩ የስለት መሳሪያዎች መሆናቸውንም ነው የተገለፀው፡

የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ እንዳሉት “ የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል እና የጨረር ምርመራ መሰረት በታካሚው ሆድ ውስጥ እስክርቢቶን ጨምሮ የተለያዩ ስለት ያላቸው ቁሳቁሶች ሊገኙ ችለዋል”፡፡

ታካሚው ታራሚ እና የአዕምሮ በሽተኛ ነው ያሉት አቶ ተመስገን ምርመራው ሊደረግ የቻለው ከዕለታት አንድ ቀን እስክሪቢቶ ሲውጥ ያየ ሌላ ግለሰብ የሰጠውን መረጃ መሠረት በማድረግ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ስራ አስኪያጁ አቶ ተመስገን በታካሚው ሆድ ውስጥ የነበሩ በርካታ ሚስማሮች፤ እስክሪቢቶና ሌሎች የስለት ቁሳቁሶች በቀዶ ሕኪምና መውጣቸውንም አስረድተዋል።

ከቀዶ ሕኪምና በኋላ ታካሚው በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ጭምር፡፡

“ታካሚው መርፌንና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን በ4 ወራት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ሳይውጥ አልቀረም” ያሉት ደግሞ የቀዶ ክክምና ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር በጋሻው መለሰ ናቸው፡፡

ዶ/ር በጋሻው ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን ልዩ ባህሪያትንና ጤናቸውን መከታተል ይጠበቅባቸዋል ሲሉም ምክር አዘል አስታየታቸው አክሏል፡፡

ከቀዶ ክክምና በኋላ የስነ ልቦና ክትትል እየተደረገ በመሆኑ ታካሚው መሻሻል እየታየበት እንደሆነም ዶ/ር በጋሻው አብራርተዋል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe