በአሸባሪው ጁንታ የተደፈሩት የ85 አመቷ መነኩሴ ሽንቴን መቆጣጣር አቅቶኛል ይላሉ፤

እማሆይ የ85 ዓመት መነኩሴ ናቸው፤ ዛሬ የምንኩስና ቆባቸውን አውልቀው ጥቁር ሻሽ ጸጉራቸው ላይ ጣል አድርገዋል። የምንኩስናው ክብር፣ ስለ ሰማያዊው አለም የተውት ስጋቸው በጉልበተኞች ረክሶ ነፍሳቸውን አቆሽሾታልና የምንኩስና ምልክታቸውን አውልቀዉ ዘመድ እንደሞተበት ሰው ጥቁር ሻሽ አስረዋል።

አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን ሸዋሮቢት ከተማ መግባቱን ተከትሎ በተፈጸመባቸው በደል “ረክሻለሁ፣ ስጋዬም ነፍሴም ቆሽሿል” ይላሉ።

በሸዋሮቢት ከተማ የቀበሌ 02 ነዋሪ የሆኑት እማሆይ በላይነሽ (ስማቸው የተቀየረ) 10 ልጆችን ወልደው የሳሙ የ85 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው። ርሳቸው እንደተናገሩት፤ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ከተማዋን ተቆጣጥረው በነበረበት ወቅት የእለት ጸሎታቸውን አድርሰው ሰላም አሳድረኝ ብለው በተኙበት እኩለ ሌሊት በራቸው በድንገት ተንኳኳ።

“…ውድቅት ሌሊት ላይ በሬ ተንኳኳ። ማነህ ስለው? ክፈቺ አለኝ። ድምጹ የልጄን ድምጽ መሰለኝና ከፈትኩኝ።› ይላሉ እማሆይ፤

ሲገባ የማላውቀው ሰው ነው። እንደገባም ለምን ቶሎ አልከፈትሽም በማለት ደጋግሞ በጥፊ መታኝ። ወደቅኩ። በወደቅኩበት ጭንቅላቴን፣ ሆዴን ደጋግሞ ረገጠኝ። እባክህ ተወኝ፣ እናት የለህም በእናትህ ይሁንብህ እያልኩ ቢያዝንና ቢተወኝ ብዬ በወደኩበት ሆኜ ለመንኩት። እሱ ግን እንኳንስ ሊያዝንልኝ ቀርቶ “ሴትና ወንድ እንሁን” አለኝ። ተጫወተብኝ። አረከሰኝ” ይላሉ እያነቡ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው እማሆይ ለመቆምም ለመንቀሳቀስም አቅም አጥተዋል። እንደልብ ለመንቀሳቀስ ጉልበታቸው አልፈቅድላቸው ብሏል። ተገደው መደፈራቸው ብዙ ደም እንዲፈሳቸው አድርጓል። ከህሊና ህመሙ ባይብስባቸውም ዛሬም የእጃቸው እና የሰውነታቸው ቁስል ክፉኛ ህመም ላይ እንደጣላቸው ነግረውናል።

“…ያ ሰው መሳይ አውሬ አርክሶኝ ሄደ፤ በማግስቱ ሙሉ ቀን ከማህጸኔ ደም ሲፈሰኝ ዋለ። አካላቴ ሁሉ ደቋል፤ የሰውነቴ ህመም አሁንም ድረስ አለ” ያሉት እማሆይ በላይነሽ፤ ወገባቸውን እንደሚያማቸው፣ ሽንታቸውን መቆጣጠር እንደተሳናቸው፤  ማህጸናቸው አካባቢ ህመም እንደሚሰማቸው ገልጸውልናል።

ቆመው ለመራመድ መቸገራቸውንና በሰው ድጋፍ እየተንቀሳቀሱ ነው።

እስካሁን ህክምና እንዳላገኙ የጠቆሙት እማሆይ፤ “እዚህ ያደረሰኝ ፈጣሪ ለወደፊቱም እርሱ ያውቃል” ሲሉም ሲቃ እየተናነቃቸው የሚያሳስባቸውን የነፍሳቸውን መንገድ ነግረውናል።

“አሁንማ ምንኩስናዬም ፈረሷል፤ አረከሰኝ፤ እንግዲህ ለነፍስ አባቴ ተናግሬ፣ እንደ ህጻን ዳግም ክርስትና መነሳትና ንስሃ መግባት አለብኝ” ብለውናል።

ከአማራ ህዝብ ጋር ሂሳብ ሊወራርድ፣ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ወረራ የፈጸመው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ህዝቦች ላይ ወረራ ከፈጸመ በኋላ ሊታሰቡ እንኳን የሚከብዱ ግፎችንና ጭካኔዎችን ፈጽሟል።

ከዚህ ቀደም በሰሜን ሸዋ በቡድን የተደፈሩ አዛውንት እናቶች መኖራቸውን እና ከእናቶች አንዷም የልጃቸውን አይን ላለማየት ራሳቸውን ማጥፋታቸውን መዘገቡ ይታወሳል።

SourceEPA

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe