ከቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ ደካማ ፖለቲከኛ የተባሉት የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር በኢራን ላይ እርምጃ ወሰዱ፡፡ ይህ የአውስትራሊያ እርምጃ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተወደ እርምጃ እንደሆነም ተሰምቷል፡፡
ኢራን ይህ እርምጃ እንዲወሰድባት የሆነችው በአውስትራሊያ ምድር ባለፈው ዓመት የጸረ ሴሜቲክ ሁለት ጥቃቶች እንዲፈጸሙ በማድረጓ ነው ተብሏል፡፡
ይህን መሠረት አድርጎም በሲዲኒ የሚገኙት የኢራኑ አምባሳደር አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ 7 ቀናት ብቻ ተሰጥቷቸዋል፡፡
አውስትራሊያ እዚህ ውሳኔ ላይ እንድትደርስ ያስገደዳት ባለፈው ዓመት በምድሯ ላይ ሁለት የጸረ ሲማዊነት ጥቃት በአይሁዶች ከተፈጸመ በኋላና የጥቃቱም የምርመራ ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ነው፡፡
በሁለቱም ጥቃቶች ውስጥ የኢራን እጅ እንዳለበት በምርመራ መረጋገጡ ይፋ ተደርጓል፡፡ ከዚህ በኋላ ሳያውል ሳያድር በኢራን ላይ እርምጃ ወስዳለች፡፡
ወራቶችን የፈጀው የምርመራ ሪፖርት እንደሚያሳየው በአውስትራሊያ ምድር ላይ የጸረ ሲሜቲክ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ ቴህራን በቀጥታ ዕዛዝ በመስጠት ተሳትፋለች፡፡
በጥቅምት እና በታህሳስ በአውስትራሊያ የተፈጸሙት ጥቃቶች ምንም የሰው ጉዳት የተመዘገበባቸው ባይሆኑም፤በንብረት ላይ ግን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ጥቃቶች ነበሩ፡፡
አውስትራሊያ በቴህራን የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን ጠርታለች፡፡ በተጨማሪም የኢራንን አብዮታዊ ዘብ ኃይል በሽብርተኝነት ፈርጃዋለች፡፡
እስራኤል ከዚህ የአውስትራሊያ ውሳኔ በኋላ የኢራን አስተዳደር ስጋትነቱ ለአይሁዶች እና ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን አውስትራሊያን ጨምሮ ለመላው ዓለም ነው እናም የኢራን አብዮታዊ ዘብን በሽብርተኛነት መፈረጅሽም ትክክል ነው ብላለች፡፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የኢራን ጦር አንዱ አካል ሲሆን፤በቀጠናው በሚደረጉ ዘመቻዎች ላይ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ዘብ እንደሆነ ይታመናል፡፡ አውስትራሊያ ይህንን ሃይል ነው በሽብር ፈርጄዋለሁ ያለችው፤በአንጻሩ ቴህራን ድርጊቱን እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡ አውስትራሊያ ይህን ውሳኔ የወሰነችበት ጊዜ ከምንም በላይ ጉዳዩን በተለዬ መንደገድ እንዲታይ አድርጎታል፡፡
አውስትራሊያ በጋዛ ያለውን ሁኔታ ካወገዘች በኋላ እንዲሁም ለፍልስጤም የአገርነት እውቅናም ለመስጠት እያሰበች እንደሆነ በለጸች ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው ይህን ማለቷ የተሰማው፡፡//

