የከተማው የመሬትና ልማት አስተዳደር ቢሮ ለጨረታ ካቀረባቸው 427 ቦታዎች ውስጥ በካሬ የቀረበው ከፍተኛ ዋጋ 265ሺ ብር መሆኑ ሲገለጽ፤ቦታውም ካዛንችስ መሆኑ ታውቋል፡፡ ዝቅተኛ ዋጋ የቀረበው ደግሞ በካሬ 10ሺ ብር ነው ተብሏል፡፡
ለአምስተኛ ዙር እየተካሄደ በሚገኘው የመሬት ሊዝ ጨረታ 18 ሔክታር መሬት ቀርቧልም ተብሏል፡፡
እስካሁን በአምስት ክፍለ ከተሞች በተደረገው የጨረታ ሂደት 76 ተጫራቾች በጊዚያዊነት ጨረታውን ማሸነፍ መቻላቸውን የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክተር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በአራተኛ ዙር በተካሄደው ጨረታ 14 ሔክታር መሬት ቀርቦ 3.6 ቢሊየን ብር ቅድመ ክፍያ ተገኝቷል መባሉም ተሰምቷል፡፡
ለአምስተኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በኮልፌ ቀራኒዮ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች 96 ቦታዎች ቀርበው 200 ተጫራቾች በጨረታ ሊዝ መመሪያ መሠረት ተገቢውን መስፈርት ባለሟሟላታቸው ከጨረታ ውጭ ሆነዋል ሲባል፤14 ቦታዎችም በቂ ተጫራቾች ባለመቅረባቸው ጨረታው መሰረዙ ተነግሯል፡፡/

