በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት 44 ተሽከርካሪዎች መሰረቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከከባድ ስርቆቶች መካካል አንዱ የሚባለው የተሽከርካሪ ስርቆት ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት በከተማዋ 44 መኪኖች መሰረቃቸውን ሪፖርት መደረጉን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዘርፍ ኋላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ በተለይም ተናግረዋል።

<የጅማ ዩኒቨርሲቲ በ19 ሚሊዮን ብር የገዛው ህንፃ ካርታ ተሰወረ ተባለ>

ባለፈው 2012 አመት ተመሳሳይ የስድስት ወራት ሪፖርት 85 ተሽከርካሪዎች ስርቆት ተፈፅሞ የነበረ ሲሆን ከ2013 ስድስት ወራት ጋር ሲነጻጸር በ41 ተሽከርካሪ ያህል ስርቆቱ ቀንሷል። ሆኖም በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ላይ መኪና ተሰርቆብናል የሚሉ ሪፖርቶች እየተበራከቱ ይገኛል።

ከሌሎች ክፍለከተሞች ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የቦሌ ክፍለከተማ ከፍተኛ የስርቆት ድግግሞሽ ከተገመዘገበባቸው መካከል ቀዳሚ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል ሲሉ ኢንስፔክተር ማርቆስ ይናገራሉ። ይህ በመሆኑም በቦሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥጥር ለማድረግ ዝግጅታችንን ጨምርሰናል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe