በአዲስ አበባ ናይት ክለቦች ፖሊስ አፈሳ አካሔደ

አዋዜ ከአዲስ አበባ እንደሰማው ከሆነ ትናንት ቅዳሜ ከተማዪቲ አልጨፈረችም።በዕለተ ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ገደማ ቦሌ አካባቢ የነበረ አንድ የምሽት ጭፈራ ሲቪል የለበሱና የፖሊስ ዩኒፎርም ያደረጉ የታጠቁና ዱላ የያዙ ወደ 10ፖሊሶች ዘው አሉ።ሁሉም ባለበት እንዳይነቃነቅና ሞባይልም እንዳያወራ አዘዙ።

ይህንን የጣሱ ሁለት ሰዎች ክፉኛ ተደበደቡ ብሏል ምንጩ ለአዋዜ።ድንገት ከታገቱት የምሽት ደስተኞች አንዱ “ለምን፣ምንድነው ምክንያቱ?” በማለት መፋጠጥ በመጀመሩ ፖሊሱ መሳሪያውን አውጥቶ ደቀነበት።አብሮት የነበረው ጓደኛው ፖሊሱን በመለመን ሁኔታውን አረጋጋው።ድንገት በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በቱሪስትነት የመጡ ፈረንጆችና በበነጋታው የቀዶ ጥገና ቀጠሮ ያለው መሆኑን የገለፀ ዶክተርም ይገኝበታል።

በመጨረሻ ያ ሁሉ ሰው ውጭ ወደጠበቀው አውቶብስ ውሥጥ ከታጨቀ በኋላ ከከተማይቱ ክፍለ ከተማዎች መካከል በአንዱ ወደሚገኝ አንድ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ተወሰዱ።እዛ ሲደርሱ እንደነሱ ከየክለቡ የታፈሱ በድምሩ 8000የሚሆኑ ስዎች ግቢው ውስጥ ፈሰዋል።አደሩ።ሌሊት ላይ ስማቸው፣ብሔራቸውና ኅይማኖታቸው እየተመዘገበ ጠዋት ላይ ተፈቱ።

አዋዜን ይሄን ወሬ ከፌዴራል ፖሊስ የሚሰጥ መግለጫ ይኖር ይሆን በማለት እስካሁን ቢያዘገየውም ከሀገሪቱ ሚዲያ በኩል ስለዚህ “የምሽት ክበቦች ድንገተኛ አፈሳ” ምንም ማረጋገጫ አላገኘም።የወሬው ምንጭ በቦታው የነበረ፣የታፈሰና ማንነቱ ተመዝግቦ የተፈታ ምንጭ እንደሆነ አዋዜ እርግጠኛ ነው ለምን ይሆን ?ምንድን ብር ምክንያቱ?ዛሬስ ናይትክለቦች ክፍት ናቸው ዝግ?

ምንጭ፡ አዋዜ

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe