በአዲስ አበባ አንድ ኪሎ ኮረሪማ ከ2ሺ ብር በላይ እየተሸጠ እንደሆነ ተሰማ

በአዲስ አበባ አንድ ኪሎ ኮረሪማ ከ2ሺ 600 ብር በላይ እየተሸጠ እንደሆነ ተሰማ፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ የንግድ መደብሮች ላይ ኮረሪማ በከፍተኛ ዋጋ ጭማሬ እንዳሳየ ታውቋል፡፡

በዚህ ስዓት የአንድ ኪሎ ኮረሪማ ዋጋ ከ2ሺ600 እስከ 700 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡ የኮረሪማ ዋጋ ከፍተኛ አምራች በሆኑ አካባቢዎች ሳይቀር ከሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ለውጥ አምጥቷል ሲል ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል 17 ወረዳዎች ኮረሪማ በስፋት ይመረታል፡፡ በእነዚሁ አካባቢዎችም የአንድ ኪሎ ኮረሪማ ዋጋ በዚህ ስዓት ከ1ሺ600 ብር በላይ እየተሸጠ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡ ይህም ቀድሞ ከነበረበት ዋጋ ከፍተኛ ጭማሬ ታይቷል ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe