በአዲስ አበባ ከመሬት ጋር በተያያዘ  የሁከት የወገድልኝ ማመልከቻን ፍርድ ቤቶች እንዳይመለከቱ የሚያግድ ህግ መዘጋጀቱ ተሰማ፤ 

በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰቶችን በተሻለ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታወቀ።

በከተማ አስተዳደሩ የደንብ መተላለፍ በዓይነትና በቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ አዲስ የቁጥጥር ስልት ተግባራዊ ማድረግ ማስፈለጉን አስታውቋል።

ለደንብ ማስከበር በችግርነት ከሚነሱት መካከል የህዝቡ ተሳትፎ ማነስ፣ የአንዳንድ ደንብ ተቆጣጣሪዎች የግንዛቤ ማነስና የስነ ምግባር መጓደል እንዲሁም የአንዳንድ አስፈፃሚ አካላት ጣልቃ ገብነት ይጠቀሳሉ።

የደንብ ጥሰት ሲያጋጥም በጊዜያዊነት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የችግሮቹ ምንጭ ላይ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት አለመስራት ሌላው ችግር መሆኑ ተገልጿል።

የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ፉፋ÷ የደንብ መተላለፍ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት አዲስ የአሰራር ስርአት መዘርጋት ማስፈለጉን እና ለዚህም በሰው ኃይል እስከ ታችኛው እርከን በባለስልጣኑ አዲስ አደረጃጀት ተሰርቶ መጠናቀቁን ጠቁመዋል፡፡

ይህም የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያግዛል ያሉት ምክትል ሥራ አስኪያጁ ÷ ባለስልጣኑ የሚመራበት ደንብ በረቂቅ ደረጃ ተዘጋጅቶ ለፍትህ ቢሮ መላኩን እና ደንቡን ተከትሎም መመሪያ እንደሚዘጋጅ አንስተዋል፡፡

የደንብ ማስከበር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ሰሞኑን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል በተደረገ አውደ ጥናት ላይ ፍርድ ቤቶች በሁከት ይወገድልኝ ስም የሚቀርብላቸውን ማመለከቻ ያለምንም ማጣራት እግድ መስጠታቸው አግባብ ባለመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ  በህግ ሊታገድ እንደሚገባ ተገልፃል፤

የፍርድ ቤቶችን ስልጣን የከተማ አስተዳደሩ በህግ ስም ሊያግድ መወሰኑ የፍርድ ቤቶችን ነፃነትና ስልጣን መጋፋት ስለመሆኑ የህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe