በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የወባ በሽታ ተከሰተ

በአዲስ አበባ በከተማዋ ባሉ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የወባ በሽታ የተከሰተ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በለሚ ኩራ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስልክ ላፍቶ እና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ግን ያለው ስርጭት ወረርሽኝ በሚያስብል ደረጃ መሆኑ ተገልጻል።

በወባ በሽታ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ ሞት ባይኖርም በጽኑ የታመሙ ሰዎች መኖራቸው ተጠቁሟል።

ወቅቱ ከመቼውም በላይ ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ በአዲስ አበባ እየተከሰተበት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሱን እዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በ2015 ዓ.ም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በአጠቃላይ 2 ሚሊየን ሰዎች ምርመራ አድርገው 648,127 ሰዎች ላይ የወባ በሽታ እንደተገኘባቸው እና ስርጭቱ በተለይም በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በክፍተኛ ሁኔታ መታየቱን  ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe