በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ጥቃቶችን ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ796 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከከሃዲው የህወሃት ጁንታ ቡድን ተልዕኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ የተለያዩ ጥቃቶችን ለመፈፀም እና የፀጥታ መደፍረስ እንዲከሰት አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ796 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በኮሚሽኑ የልዩ ልዩ ህገ- ወጥ ዝውውር ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር ግርማ ተሰማ እንደገለጹት ቡድኑ ላለፉት 27 አመታት የዘረጋውን የግንኙነት መረብ ተጠቅሞ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ሊፈፅም ያሰበው የሽብር ጥቃት እንዳይሳካ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በተደረገ ጠንካራ የክትትል እና የቁጥጥር ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
ከከሃዲው የህወሃት ጁንታ ተልዕኮ ተቀብለው የተለያዩ ጥቃቶችን ለመፈፀም እና የፀጥታ መደፍረስ እንዲከሰት አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 796 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ኮማንደር ግርማ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም በርካታ የጦር መሳሪዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶች በፍርድ ቤት የመበርበሪያ እና የመያዣ ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች እና የሚከሰቱ ግጭቶች በህወሃት ፊት አውራሪነት እና ድጋፊ ሰጪነት የሚፈፀሙ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጡ እና ሃይማኖትን ከሃይማኖት፣ ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት የተዘጋጁ ሰነዶች በብርበራ ወቅት መገኘታቸውን ኮማንደር ግርማ አስረድተዋል፡፡
የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ጭምር የጁንታውን ቡድን ተልዕኮ በአዲስ አበባም ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ እና ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስታወሱት ኮማንደር ግርማ ተሰማ በተለያዩ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት እና በልዩ ልዩ ተቋማት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 202 የተለያዩ የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳት ተይዘዋል ብለዋል፡፡
የደንብ አልባሳቶቹ በሃይማኖት አባቶች መኖሪያ ቤቶች ጭምር መገኘታቸውን የጠቀሱት ኮማንደር ግርማ ይህ ደግሞ ህገወጡ እና ከሃዲው የህወሃት ቡድን በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሳይቀር ሰርጎ በመግባት ግጭት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሰ አንደሚገኝ የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ለተገኘው ውጤት የህብረተሰቡ ተሳትፎ የጎላ ሚና እንደነበረው ያስታወሱት ኮማንደር ግርማ ተሰማ አዲስ አበባ ላይ ጀምረን አዲስ አበባ ላይ እንጨርሰዋለን በሚል ከንቱ ምኞት ላይ ታች ሲሉ ህልማቸው የመከነባቸው የጥፋት ቡድኖች ምንም አይነት ቀዳዳ እንዳይኖራቸው እና በተለያዩ ተቋማት እና አካባቢዎች ተሰግስገው የሚገኙ ሌሎች የጥፋት መልዕክተኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe