በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የመሬት ይዞታ ማህደሮች ዲጂታላይዝ ተደርገዋል ተባለ

የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በስድስት ወራት ውስጥ በሰራው የሪፎርም ስራ በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም የይዞታ ማህደሮችን ዲጂታላይዝ ማድረጋቸውን አስታወቀ። የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን ለስድስት ወራት የሪፎርም ስራ ሲሰራ ቆይቶል።

በዚህም በ 11ዱም ክፍለከተሞች የሚገኙ 670 ሺህ 568 የይዞታ ማህደሮችን ዲጂታላይዝ የማድረግ እና እንደአዲስ ተቆጥረው እንዲታወቁና አዲስ ኮድ እንዲሰጣቸው በማድረግ ተደራጅቷል።

በተካሄደው የሪፎርም ስራ ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲሁም የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራርና ሌብነት ለመፍታት የሚያስችሉ የህግና መመሪያ የማሻሻል ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን 27 የሚሆኑ አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት የሚያስችል ሲስተም ተግባራዊ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

 

SourceVia EPA

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe