በአዲስ አበባ የሞተን ዶሮ ባልተፈቀደ ቦታ ላይ መጣል እስከ 25ሺ ብር ያስቀጣል ተባለ

በአዲስ አበባ የሞተ ዶሮን እና ሌሎች እስሳትን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል 25ሺ ብር ያስቀጣል ተባለ፡፡ የአጥንትና የስጋ ተረፈ ምርቶችንም እንዲሁ ባልተፈቀደ ቦታ የጣለ ድርጅት 50ሺ ብር እንዲሁም ግለሰብ ከሆነ ደግሞ 5ሺ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

ለዓመት በዓል መዋያ ብለው በ800 ወይም በ1000 ብር የገዙት ዶሮ አያድርሰውና ከመታረዱ በፊት ሞት ቢቀድመው በንዴት ያልሆነ ቦታ እንዳይጥሉት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበዋታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ደንብ ተላልፈው ከተገኙ ግን የ25ሺ ብር ቅጣት ይጠብቅዎታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከቤት እስሳት የሚወጡ እዳሪ እንዲሁም የእስሳት የምግብ ተረፈ ምርቶችን ባልተፈቀደ ቦታ የጣለ አልያም አካባቢውን ያቆሸሸ ማንኛውም ሰው በ50ሺ ብር ይቀጣል የተባለ ሲሆን ፡የተለያዩ እንስሳትን ባልተፈቀደ ቦታ በማጸዳዳት አካባቢውን ያቆሸሸ ደግሞ በ5ሺ ብር ይቀጣል፡፡

እነዚህን ቅጣት የሚያመጡት ደንቦች በደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ.ም ተደንግጎ እንደሚገኝ ከሸገር ሬዲዮ ዘገባ ላይ ተመልክተናል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe