በአዲስ አበባ የወይ ብላ ማርያም ታቦትን ለመሸኘት በወጡ ምዕንመናንና ፖሊስ በተፈጠረ ግጭት የ3 ሰው ህይወት አለፈ

መንግስት  ችግር የፈጠሩ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እሰራለሁ ብሏል፤

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ እና ቡራዮ አዋሳኝ ቦታ የምትገኘውን የወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን ታቦት ከጥምቀተ ባህር ወደ ደብሩ እየተሸኘ ባለበት ስነ ስርዓት ላይ በቡራዩ ከተማ ኢ መደበኛ አደረጃጃት ወጣቶችና በደብሩ ሰንብት ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሀከል ከባንዲራ   ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባትና ግጭት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፤

ችግሩ እንደተከሰተ የፀጥታ አካላት በስፍራው የተገኙ ሲሆን ፖሊስ በተኮሰው የአስለቃሽ ጭስ ሳቢያ በርካታ ምዕንመናን፤ የሰንብት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ዘማሪያን ራሳቸውን ስተው በየቦታው ለመውደቅ መገደዳቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል፤

ከዚሁ ግጭት ጋር በተያያዘ የአካባበው ደብር አገልጋይ የሆነ ስመኙው የተባለወ የ24 ዓመት  ወጣት እንዲሁም የቡራዩ ከተማ ሌላ ወጣት በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው አልፏል፤ የወጣት  የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት በወይበላ ማርያም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሃላፊ ብዕዕ አቡነ መልከ ፀዲቅ በተገኙበት ተፈፅሟል፤

ትላንትና በተፈጠው ግጭት ሳቢያ የወይብላ ማርያም ታቦት ወደ ማደሪዋ መግባት ሳትችል ቀርታ በአቅራቢያው በሚገኘው ቀራኒዮ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ለማደር መገደዷ ታውቋል፤

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አግልግሎት በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ በተፈጠረው ችግር በሰዎች ላይ ሞትና ከባድ ጉዳት መድረሱን አሳውቆ በዓሉ በተገቢው መንገድ ባለመከበሩ፣ እንዲሁም በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማው ገልጿል፡፡

የችግሩን መንስኤ  በማጣራት ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለሕግ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፤

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፖርቲ ትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የጸጥታ ሀይሎች በሰላማዊው ህዝበ ክርስቲያን ላይ የወሰዱትን የሀይል ጥቃት አውግዞ መንግስት አጥፊ የፀጥታ አባላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe