በአዲስ አበባ 7 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተከል ተገለፀ

በአዲስ አበባ የተለያየ አካባቢ ነዋሪ ወጣቶች የሚመራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር የተጀመረ ሲሆን በዚህ መርሀግብር 7 ሚሊየን ችግኝ የሚተከል ይሆናል።

የተለያየ አካበቢ ነዋሪ ተወካዮች የሆኑ ወጣቶቹ ከኢ/ር ታከለ ኡማ በመሆን በዛሬው እለት ችግኝ የተከሉ ሲሆን በቀጣይም ወጣቶቹ በሚኖሩበት አካባቢ በተዘጋጀ ቦታ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎችን በማስተባበር ችግኞች እንዲተከሉ የሚያደርጉ ይሆናል።

Read also:የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከአስር ዓመት በኋላ 2200 በላይ ይደርሳል ተባለ

ከ50 ሠፈር በላይ የተውጣጡት ወጣቶቹ ችግኞቹን የመንከባከብና እድገታቸውን የመከታተል ኃላፊነትም ወስደዋል።

ኢ/ር ታከለ ኡማ ወጣቶቹ አረንጓዴ አሻራቸውን ለማሳረፍ በመዘጋጀታቸው አመስግነዋል።እንደ ችግኝ ተከላው ሁሉ ወጣቶች የከተማዋ ልማትና ኢኮኖሚ ዋና ተዋናይና ተሳታፊ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ነው ብለዋል።በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በአዲስ አበባ 7 ሚሊየን ችግኝ የሚተከል ይሆናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe