ዋጋቸው ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆኑ መድሃኒቶችንና የህክምና መሳሪያዎችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ተከለከለ፡፡
መድሃኒት አስመጭዎች በሀገር ወስጥ የሚመረቱ መድሃኒቶችን ከትላንት ጀምሮ ከውጭ ማስገባት እንደማይችሉም ተነግሯል፡፡
በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድሃኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎችን ከውጭ ማስገባት ተከለከለ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጽያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት በማዕከል የሚፈጸሙ የመድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ይፋ አድርጓል፡፡
ከትላንት ጀምሮ ተፈጻሚ በሚሆነው መመሪያ መድሃኒት ወይም የህክምና መሳሪያ በአገር ውስጥ አምራች የሚመረቱን በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም እንደማይቻል ይደነግጋል፡፡
መድሃኒቱ ወይም የህክምና መሳሪያው በአገር ውስጥ አምራቾች የማይመረትም ቢሆን ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ከሆነም ከውጭ መግዛት እንደማይቻል በመመሪያው ተቀምጧል፡፡ ሆኖም የአገር ውስጥ አምራቾች አቅም በቂ አለመሆን ወይም ግዥው በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ መፈጸሙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ማስገኘቱ ሲረጋገጥ ሊፈቀድ እንደሚችል መመሪያው ደንግጓል፡፡
በተጨማሪም የውጭ አገር ተጫራቾች ካልተሳተፉበት ውጤታማ እንደማይሆን ከታመነ እንደሚፈቀድ ያብራራል፡፡

