በኢትዮጵያ ማስክ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ ፀደቀ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጭ በሁሉም ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ መፅደቁን አስታወቁ።

በብራዚል የነበረው መዘናጋት እና ቸልተኝነት ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ፥ አሁን ላይ ህጉን ማጥበቅ አስፈላጊ መሆኑን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

“ለራስ፣ ለቤተሰብ፣ ለወገን እና ለሀገር ብለን ከሌሎች ስህተት በመማር ጥንቃቄያችንን እናጠናክር” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህብረተሰቡም ለራሱ ሲል በመንግስት እና በባለሙያዎች የሚተላለፉ የጥንቃቄ መመሪያዎችን ችላ ሳይል እንዲተገብርና ለህግ አስከባሪው አካል እንዲታዘዝም ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe