የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት እንደገለጸው በኢትዮጵያ በቀን 9 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡
በፍጥነት ማሽክርክር ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ የብዙኃን መገናኛ ንቅናቄ ማብሰሪያ ፕሮግራም በኢሊሊ ሆቴል በተካኼደበት መርሐግብር ይፋ በተደረገ መረጃ በኢትዮጵያ በቀን 9 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ።
የብዙኃን መገናኛ ንቅናቄው ለእንድ ወር የሚቆይ ሲሆን በፍጥነት ማሽከርከር ላይ ያተኮሩ የምስል እና የድምፅ ማስታወቂያዎች በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት አየር ላይ ይውላሉ። መልዕክቶቹ በማህበራዊ ሚዲዮዎች በህትመት ውጤቶች እና ሌሎች የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች አማካኝነት እንዲተላለፉ ይደረጋል። በተጨማሪም የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር እና የጎዳና ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄው ማብሰሪያ ስነ-ስርዓት ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች: የባለድርሻ አካላት ተወካዮች የሚዲያ ተቀማት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በኢሊሊ ሆቴል ተከናውኗል።
በ2016 ዓ.ም በትራፊክ አደጋ 3 ሺ 111 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን በመድረኩ ላይ የቀረበ ሪፖርት ያመለከተ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም በቀን ወደ 9 ሰዎች በአደጋ ሕይወታቸውን የሚያጡበት አሳዛኝ ሁኔታ እየታየ መሆኑ ተነግሯል።
በ2016 ዓ.ም በአደጋው ከ10 ሺ በላይ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ከ4 ቢልየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
በኢትዮጵያ 1 ነጥብ 5 ሚልየን ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን፣ የሰው ተሽከርካሪ ጥምርታ 10 ተሽከርካሪ ለ1000 ሰዎች መሆኑ የተመለከተ ሲሆን በ2016 ተሽከርካሪ 67ሺ 633 ሲሆን የደረሰው አደጋ ግን 45 ሺ 571 ነው ይላል።
የትራፊክ አደጋ ዋንኛ መንስኤ ፍጥነት እና የመንገድ ሥርዓት አጠቃቀም አለመዳበር ናቸው ተብሏል።(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)
በኢትዮጵያ በቀን 9 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጣሉ

