በኢትዮጵያ በአራት አመት ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ዕቅድ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጠቆሙ።በጪው ክረምት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በ2011 ዓ.ም ክረምት ወቅት ከተካሄደው የችግኝ ተከላ በኋላ እና በ2012 ክረምት የሚካሄደውን የችግኝ ተከላ የዝግጅት ስራዎች የተመለከተ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተደረገ ነው።
Read also:በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ ላይ የተመዘገበው የባሌ ተራራሮች ብሔራዊ ፖርክ አደጋ ላይ…
በውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድር፣ የሚዲያ ሃላፊዎች፣ አርቲስቶች፣ አትሌቶችና በተለያዩ ዘርፎች ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦች ታድመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የተጀመረውን የችግኝ ተከላ ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
Read also:ፈረንሣይ በ50 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ለኢትዮጵያ የሳተላይት ማምረቻና መገጣጠሚያ ማዕከል ልትገነባ…
በአራት አመት ጊዜ ውስጥ 20 ቢሊዮን የዛፍ ችግኝ ለመትከል መታሰቡን ገልጸው፤ ”ይህ እውን ሊሆን የሚችለው የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ሲቀጥል ነው” ብለዋል።
በእንጦጦና በተለያዩ አካባቢዎች የታየው ለውጥ ዛፍ በመተከሉ የመጣ በመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።
በመጪው ክረምት የታቀደውን 5 ቢሊዮን የዛፍ ችግኝ የመትከልን ስራ ለመደገፍ በርካታ አካላት ፍላጎት እንዳሳዩም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ባለፈው ክረምት ከተካሄደው የችግኝ ተከላ በኋላ እና በመጪው ክረምት የሚካሄደውን የችግኝ ተከላ የዝግጅት ስራዎች በተመለከተ ለውይይት የሚሆን መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ባለፈው የተገኙ ልምዶች መቀመራቸውን ተናግረዋል።
Read also:ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክያት ከ139 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ባለይ የሚገመት…
ባለፈው ክረምት ከተተከሉ 4 በሊዮን ችግኞች ውስጥ 84 በመቶ የሚሆነው መጽደቁን እንዲሁም የመንከባከብ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
በመጪው ክረምት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ ለዚህም ስራ 602 ሚሊዮን ብር በጀት የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል።
የአመራር ለስራው ትኩረት መስጠት፣ የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ስራውን ውጤታማ እንዳደረገው ገልጸው፤ የድህረ ተከላ ክትትል ውስንነት፣ የዝግጅት ጊዜ ማጠርና የተከላ ጉድጓድ ቦታዎች ልየታ ባለፈው የታዩ ክፍተቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል።
Read also:በአረንጓዴ አሻራ ከተከተሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ…
ባለፈው ክረምት ከ4 በሊዮን በላይ የዛፍ ችግኝ የተተከለ ሲሆን 23 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ተሳትፎ ማድረጋቸው ይታወሳል።