ይልቅ ወሬ ልንገርህ:- ሠላም – በኢትዮጵያ ከባንክ ሊገኝ ስለመሆኑ

ለመሆኑ ስለ ሠላም ባንክ ምስረታ በሀዋሳ መካሄዱን ሰምተሃል? አልሰማሁም ነው ያልከኝ? የዛሬ ሁለት ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ሚኒስቴርን አዋቅረው በሚኒስትርነት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ሲሰይሙ በዓለም ላይ የመጀመሪያው በሚኒስትር ደረጃ የተቋቋመ መስሪያ ቤት ተብሎ ነበር፡፡ እናስ? እናማ የሰላም ሚኒስቴር መቋቋሙ ሳይሆን በውስጡ ተጠሪ ተብለው የተሰጡት መስሪያ ቤቶች ከአቅሙ በላይ በመሆናቸው የታሰበውን የሰላም በሀገሪቱ ላይ ማምጣት ሳይችል ቀርቷል፡፡

ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር የሚመራቸውን መስሪያ ቤቶች እነማን እንደሆኑ አውቀሃል? ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት፤ ፌደራል ፖሊስ፤ኢሚግሬሽንናና የዜግነት ጉዳዮች ባለስልጣን፤ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፤የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ፤ ስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ባላስልጣን  ወዘተ በየራሳቸው ከፍ ያለ ሀገራዊ ሀላፊነት ያላቸው መስሪያ ቤቶች በሰላም ሚኒስቴር ስር ከሆኑ በኋላ ሰላም አደፍራሽ አካላት አመቺ ሁኔታ ተፈጠረላቸው መሰለኝ ሰላሙን እንደልባቸው ማደፍረሱን ተያያዙት፡፡ እንደውም የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ሰሞኑን አጠናሁትብሎ ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ሰላም ማስከበርና የሰላም ግንባታ ላይ መስራት በተለያየ መስሪያ ቤቶች መከወን ሲገባው ለሰላም ሚኒስቴር በመሰጠቱ ሀላፊነቱን ሊወጣ አላስቻለውም፤ እናም የመስሪያ ቤቱ አወቃቀር እንደገና ይታይ ስለማለቱ ተሰምቷል፡፡

<ይልቅ ወሬ ልንገርህ:- ስለ ታማኝ በየነ ‹ሿ ሿ›>

‹የቸገረው እርጉዝ ያገባል› እንዲሉ ሰላም ሚኒስቴር ያቃተውን ሰላም በሀገሪቱ የማስፈን መላ እኔ እከውነዋለው ያለ አንድ ግለሰብ ሰላምን ከባንክ እንድናገኝ ‹ሰላም ባንክን› በአዋሳ ከተማ መስርቷል፡፡ ባለፈዉ ማክሰኞ በይፋ የተመሠረተዉ ማዕከል የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢን በሚያዉከዉ ግጭትና ጥቃት ሰበብ የደፈረሰዉን ሠላም ለማጥራትና ለማርጋት የሚደረጉ ጥረቶችን ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ተብሏል ባንኩ።

በኢትዮጲያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚረዱ የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያሰባስብ፣ የሚያከማችና ሥራ ላይ የሚያዉል ነው አዋሳ[1]ዉስጥ ተመስርቷል «የሰላም ባንክ» ።በአንድ ግለሰብ ሐሳብ አመንጪነት የተመሰረተዉ የሰላም ባንክ ዘር፣ ፆታ፣ እድሜና የትምሕርት ደረጃ ሳይለይ ሁሉንም ኢትዮጵያ በአባልነት የሚያቅፍ እንደሆነ ተነግሯል። ይህንን የሰማ አንድ ወዳጄ ምን ቢል ጥሩ ነው? እንግዲህ ከዚህ በኋላ ሰላም የሚሻ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የባንክ ቡክ ከፍቶ ከባንኩ መበደር አልያም በአነስተኛ ወለድ መበደር ይችላል ሊልስ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe