በኢትዮጵያ ከጦርነቱ በፊት የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲጣራ ተወሰነ፤

የድርጅቱ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጽ/ቤቱን በኬኒያ ከፍቷል፤

በሰሜን አሜሪካ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ድርጅት ክስ ያቀረበባቸው ግለሰቦች ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ከፍተኛ ኮሚሽን እንዲታይ መወሰኑን ዐስታወቀ።

ድርጅቱ፦ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖት እና ብሔር ተኮር ጭፍጨፋ እና እንግልት የፈጸሙ ሲል በዘር ማጥፋት በመጠርጠር ክስ ያቀረበባቸው ግለሰቦች ጉዳይ በጦርነቱ ምክንያት ከደረሱ የመብት ጥሰቶች ጎን ለጎን በኮሚሽኑ እንዲታይ መወሰኑን ገልጧል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ከፍተኛ ኮሚሽን ውሳኔ ተወስኖ በኢትዮጵያ ከጦርነቱ ጋር በተገናኘ ምርመራ እንዲያደርግ በድምፅ ብልጫ ፀድቆ ኮሚሽኑ  በኬኒያ ጽ/ቤት ከፍቶ ስራ መጀመሩን የገለፁት  የድርጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ አቶ ተፈራ ደምሴ  የእኛ ጥያቄ ደግሞ ከጦርነቱ ጋር ባልተያያዘ ደግሞ ከዚያ በፊት የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ስላሉ እሱም አብሮ ይታይልን  የሚል ነው ብለዋል፤

ድርጅቱ ተጨማሪ ራፖርተሮች መድቦ አንድ ላይ ሥራ ይጀምርልን በሚል ያቀረብነው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷዋል ያሉት አቶ ተፈራ  የዘር ማጥፋት ወንጀል ምርምራው ከዚህ ጋር አንድ ላይ ጎን ለጎን ይታያል ብለዋል።

አቶ ተፈራ ደምሴ ድርጅቱ ወንጀል ፈጽመዋል ያላቸው ግለሰቦችን ጉዳይ የሚመለከቱ መረጃዎችን በመሰብሰብ ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ከሕግ ባለሞያዎች ጋር በመሆን ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ተናግረዋል። አክለውም ኢትዮጵያውያን በሃይማኖታቸው፣ በብሄራቸውና በማንነታቸው ምክንያት የሚፈጸምባቸውን ግድያ ለማስቆም ድርጅቱ በርካታ ተግባራትንም ማከናወኑን መግለጣቸውን  ዶይቸ ቬሌ ዘግቧል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe