በኢትዮጵያ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ ህፃናት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች ናቸው ተባለ

በኢትዮጵያ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ ህፃናት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች ናቸው ተባለ

የፀጥት ችግር እና ግጭት;- አንበጣ መንጋ ጉዳት;- የኮሮና ቫይረስ ተፅእኖ;- የትግራይ ክልል ችግር ተደማምረው ኢትዮጵያ ውስጥ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ ታዳጊዎች እና ህፃናት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች እንዳደረጋቸው ተገለፀ።

ይህን የገለፁት UNICEF የኢትዮጵያ ቢሮ እና የስውዲን ኤምባሲ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው።መግለጫው ትኩረቱን ያደረገው በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ ችግር ፣ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ላይ ነው።በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ችግር እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ ህፃናት እና ታዳጊዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

የUNICEF የኢትዮጵያ ቢሮ ተወካይ አደሌ ሆደር የረብሻ እና የፀጥታ ችግር፣ የኮቪድ-19 ተፅእኖ፣ የአንበጣ መንጋ፣ የትግራይ ክልል ችግር ተዳምረው በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ሰብዓዊ እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 23.5 ሚሊዮን አድርሶታል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ 12.5 ህፃናት እና ታዳጊዎች መሆናቸው ችግሩን ይበልጥ አክፍቶታል ብለዋል።

ኃላፊዋ ችግሩ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል እንዳለ የገለፁ ሲሆን በተለይ ግን በትግራይ ክልል ያለው ችግር ግን ይበልጥ የከፋ ነው ብለዋል።

አክለውም ፥ “በትግራይ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ 6 ሺህ ህፃናት መረጃ በእጃችን አለ፤ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ ህፃናት ጉዳይ ብዙ አደጋ ያለው ነው ። ለተለያየ ጥቃት ሊዳረጉ ይችላሉ፣ ማንኛውም ነገር ሊደርስባቸው ይችላል፤ ልጆቹ ሊሸጡ፣ ለሌላ ሰው ሊሰጡ ይችላሉ ስለዚህ ለእነዚህ ህፃናት ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe