በኢትዮጵያ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ያለ ህጋዊ ምዝገባ እየሰሩ መሆናቸው ተነገረ፤

የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቁጥር ከ25 በላይ ደርሷል፤

በኢትዮጵያ በግለሰቦችና በሀይማኖት ተቋማት ተይዘው ሀይማኖታዊ ሰበካ የሚያከናውኑ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቢኖሩም ህጋዊ ምዝገባ አከናውነው እየሰሩ አለመሆናቸው ቅሬታ መፍጠሩ ተሰማ፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ከ25 በላይ የሚሆኑ በአብዛኛው የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ቻናሎች በኢትዮጵያ የቀጥታ ስርጭትን ጨምሮ አገልግሎት እየሰጡ ቢሆንም አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 በፖርላማ ፀድቆ እስኪወጣ ድረስ ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ እየሰሩ እንደሆነ ታውቋል፤

አዋጁ ባለፈው ኣመት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲፀድቅ የሀይማኖት ተቋማት የሚዲያ ባለቤት እንዳይሆኑ የሚከለክለውን ነባሩን አዋጅ በመሻር የሳተላይት ስርጭት ላይ ብቻ ፍቃድ አውጥተው እንዲሰሩ የፈቀደ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለአንድም የሀይማኖት የቴሌቪዥኝ ስርጭት በሚመለከተው የመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ፍቃድ እንዳልተሰጠ ታውቋል፤

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በስርጭት ላይ ላሉትም ሆነ ለአዳዲስ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች  በአዋጁ መሰረት ፍቃድ ያልሰጠው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በፖርላማ የሚሰየሙ የባለስልጣኑ የቦርድ አባላት ስራ ባለመጀመራቸው እንደሆነ የእንግሊዝኛው ሪፖርትር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

መንግስት የባለስልጣኑን ቦርድ ሹመት ያዘገየው በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ በትኩረት ማጣት እንደሆነ ሲነገር ቦርዱ ስራ ቢጀምርም የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ማመልከቻ መቀበያ መመሪያ አለመፅደቁም ሌላው ችግር መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ሀይኖታዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶችን የሚያሰራጩ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣበያዎች የሌሎችን ሀይማኖት የሚያጥላሉ፤ ሀሰተኛ ሰበካዎችንና ቅስቀሳዎችን በማስተላለፍ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች  ቅሬታዎች ሲቀርብባቸው መቆየቱ  ይነገራል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe