በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ ተመረቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ/radio therapy/ ተመረቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል:: በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰጠው ይህ የጨረር ህክምና ወረፋ በመጠበቅ ላይ ላሉ የካንስር ህመምተኞችን ችግር ይቀርፋል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሆስፒታሉ የካንሰር የጨረር ህክምና ይሰጥ የነበረ ቢሆንም አሮጌ በመሆኑ የካንሰር ህመምተኞች መስተጓጐሎች እንደነበሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሎጅ ዲን ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኘው ተናገረዋል፡፡

<ሱዳን የህወሀት የሚሊሻ መሪን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች!>

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ዛሬ የተመረቀውን የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጨምሮ በቀጣይ ጅማ፣ ኦሮሚያ፣ ኀንደር፣ ሀዋሳ እና ሀረር ሆስፒታሎች አገልግሎቱን ለመጀመር መታሰቡን ገልጸዋል፡፡

<4 ኪሎ የሚገኘው የአርበኞች ማህበር ህንፃ ሊፈርስ ነው>

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የህክምና ማእከል በማድረግ በምስራቅ አፍሪካ የህክምና ቱሪዝም ለማድረግ ቢታቀድም የበጀት እጥረት ማነቆ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ኘሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና አስረድተዋል።

ምንጭ:- የጤና ሚኒስቴር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe