በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ማሽቆልቆል እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ገለፀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ይህንን የገለፀው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን በትላንትናው እለት የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደበት ወቅት ነው።
በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ተዕግስት ይልማ እንደገለጹት፣ ምክርቤቱ በሃገሪቱ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን እራስን በራስ መቆጣጠር እንዲችሉና በስነ ምግባር ታንፀው በሃላፊነት ህዝብን የሚያገለግሉ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ምክርቤቱ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው ያሉት ሰብሳቢዋ የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት የመገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ከዘገባቸው ጋር ተያይዞ ከተለያዩ አካላት የሚደርስባቸውን ጫና በመቀነስ በከፍተኛ ሃላፊነት ስራቸውን እንዲያከናውኑ መደረጉ ከተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች አንዱ ነው ብለዋል።
ይሁን እንጂ የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ማሽቆልቆሉ እጅግ አሳሳቢ እየኾነ መጥቷል ሲል ምክር ቤቱ ትናንት ጠቅላላ ጉባዔውን በጀመረበት ወቅት ስጋቱን ገልጧል። ምክር ቤቱ፣ የመገናኛ ብዙኃን የነጻነት ምህዳር እየጠበበ መሄዱ፣ ሃሳብን በነጻነት በመግለጽ መብት ላይ ችግሮች መበራከታቸውና የጋዜጠኞች እሥርና እንግልትም አሳሳቢ መኾኑን አስታውቋል።
ይህ ኹኔታ እንዲስተካከል መንግሥትን በይፋ መጠየቁንም ምክር ቤቱ ጠቅሷል። በዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤው የ2014 እና 2015 በጀት ዓመት ሪፖርቶች እንዲሁም የ2016 ዓ.ም ዓመታዊ እቅድ ቀርቦ ከምክርቤቱ አባላት ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe