በኢትዮጵያ የዘረመል ልውጥ ህያዋን ምርት ለአምስት ዓመታት ተግባራዊ እንዳይደረግ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ ውስጥ አስፈላጊው ቅድመ-ዝገጅት ሳይደረግና የህዝብ አስተያየት ሳይጠየቅ ልውጠ ህያዋንን ለማምረትና ለመጠቀም በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት አቤቱታ ለመንግስተ አቀረቡ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ አስፈላጊው ቅድመ-ዝገጅት ሳይደረግና የህዝብ አስተያየት ሳይጠየቅ ልውጠህያዋንን ለማምረትና ለመጠቀም በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት የግብርና መስሪያ ቤት በጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም ወይም የካቲት 5 ቀን 2020 “agricultural biotechnology annual report (ET2019-0010)” የግብርና ጥበበ-ሕይወት አመታዊ ግምገማ በሚል ርእስ ያዘጋጀውን ሪፖርት መልቀቁ ይታወሳል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው ከሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ለገበያ የሚሆን የቢቲ ጥጥ እንዲመረትና እና ለአፍሪካ ተስማሚ የሆነው ብዙ ውሃ የማይፈልግው (ቆጣቢ) የበቆሎ ሰብል በተከለለ ቦታ የሙከራ ምርምር እንዲካሄድ የፈቀደች መሆኗን ይፋ አድርገዋል፡፡ የቢቲ ጥጥ ወደ ምርት መግባት ብዙ ጉዳቶች አስከትለዋል ለምሳሌ በህንድ አገር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በውጤቱ ምክንያት ራሳቸውን ለህልፈተ-ሕይወት ዳርገዋል፤ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካና ቡርኪናፋሶ የቢቲ-ጥጥ ምርት የታሰበለት ውጤት ያክል አላስገኘም፡፡

Read also:አቶ ስዩም መስፍን የባንክ ሂሳባቸውን ለማስመርመር ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

በተጨማሪ በሞንሳንቶ የቀረበው ድርቅ የሚቋቋም ልውጥ የዘረመል በቆሎ የተፈለገውን ምርት ሳያስገኝ በመቅረቱ በደቡብ አፍሪካ መንግስት ይሁንታን ተከልክለዋል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ የብዙ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ሰብሎች መገኛ እና የብዝሐ-ሕይወት ዋና ማእከል በመሆንዋ በአለም ላይ ብዝሐነት ያለው የምግብ ስርአት ካላቸው አገሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች፡፡

በኢትዮጵያ በምግብና ግብርና ላይ የታየ ብዝሐነት ሊመዘገብ የቻለው በአገሪቱ የሚገኙ በትንሽ አቅም ምግብ አምራች የሆኑ አርሶአደርች ለሺ አመታት ባዳበሩት ሩቅ አሳቢ ሰብል የማምረትና አያያዝ ስርአት ምክንያት ነበር፡፡ አሳማኝ ማስረጃዎች ባይኖሩም በአንድ በኩል የዘረመል ልውጥ ህያዋን በግዜ ሂደት ምርትና ምርታማነትን እንደሚጨምሩ፣ የእርሻ ኬሚካሎች መጠቀም እንደሚቀንሱ እና አካባቢን መሰረት ያደረጉ ተግዳረቶች እንደሚከላከሉ ይገልፃል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዘረመል ልውጥ ህያዋን ከፍተኛ የጤና ጠንቅ እንደሚያስከትሉ፣ የምግብ ይዘታቸው ደካማ እንደሆነና አካባቢውን እንደሚጎዱ የሚያሳዩ እልፍ አእላፍ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ በነዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ ከ20 ሚልዮን በላይ ለሚሆኑት ኢትዮጵያውያን እንደ ዋና ምግብነት የሚያገለግለው የእንሰት ሰብል ላይ ሙከራ መደረጉ እጅግ አሳሳቢ የሚያደርገው፡፡ ስለሆነም እንቅስቃሴው በአሁኑና በቀጣይ ትውልድ ላይ የሚኖረው የጤናና ችግሮችን የመቋቋም አቅም የሚያፋልስ የሚሆነው፡፡

Read aslo:የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከአስር ዓመት በኋላ 2200 በላይ ይደርሳል ተባለ

የዘረመል ልውጥ ህያው በኢትዮጵያ እንዲተገበር የተደረገው በትላልቅ አለም አቀፍ ተቋማት ፍላጎት ብቻ ሲሆን ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ትክክለኛ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ አለመከናወኑ፤ ገለልተኛ የሆነ የጉዳት ዳሰሳዊ ግምገማ አለመደረጉ እንዲሁም መደበኛ የደህንነተ-ሕይወት ፕሮቶኮል ሳይከተል ነበር ወደ ስራ የተገባው፡፡ የዘረመል ልውጥ ህያው ለመተግበር የሚታየው ጥድፍያ የሚያመለክተው የቁጥጥር ስርአት ተዘርግቶሎት የማህበረሰቡ ፍላጎት ሊያሟላ በተቋቋመ የመንግስት ተቆጣጣሪ አካል አማካኝነት ሳይሆን እየተተገበረ ያለው የተወሰኑ የግል ኢንዱስትሪውን ተጠቃሚዎች ፍላጎት ለሟሟላት ሲባል ብቻ መሆኑን ያሳያል፡፡

በአገራችን የዘረመል ልውጥ ህያዋን ምርት በመጠቀማችን ምክንያት ለሚፈጠረው ጠንቅ ለመከላከል ተብለው የተደራጁ ተቋማት የህብረተሰቡ ጤንነት ለመጠበቅና በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችል በቂ አቅም የሌላቸውና በስርአት ያልተደራጁ ናቸው፡፡ የፀደቀውን የደህንነተሕይወት አዋጅ ቁጥር (896/2015) ለማስፈፀምና የዘረመል ለውጥ ህያዋን በተመለከተ ፍቃድ የመስጠት ኃላፊነት የተጣለበት በጠቅላይ ሚኒስተር ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የፌደራል አካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮምሽን በሰው ሀይል ያልተደራጀና ውስን ፖለቲካዊ ድጋፍ ያለው በመሆኑ የዜጎች ፍላጎት ሟሟላት አልተቻለውም፡፡ በተጨማሪ አገራችን የምግብ፣ መድሃኒት፣ የጤና አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 661/2009 የወጣ ህግ ቢኖራትም ከሌላው አለም በተለየ መልኩ የዘረመል ልውጥ ምግቦች አጠቃቀም በሚመለከተ የፖሊሲ ማእቀፎች የላትም/አላዘጋጀችም፡፡

Read also:የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ለበረራ አስተናጋጆች ለመስጠት የወሰነው  የቋንቋ ፈተና ተቃውሞ ገጠመው

ከዚህ በዘለለ አገሪቱ ለአለም ጤና ድርጅት እንዲሁም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት ላይ አባል ለሆኑት አገራት ክፍት በሆነው የcodex Alimentarius ኮምሽን ውስጥ በአባልነት ተመዝግባለች፡፡ ይሁን እንጂ አገሪቱ የዘረመል ልውጥ ህያዋን ለመፈተሸና ምርቶችን ለመለየት የሚያስችል ዘመናዊ መሳርያዎች በሚገባ የተደራጀ አገር-አቀፍ ልዩ ቤተ-ሙከራ ባለቤት አይደለችም፡፡ ስለሆነም እኛ ለኢትዮጵያ መንግስት የምናቀርባቸው ሀሳቦች የሚከተለቱን ናቸው፡-

  1. ተቋማዊ የሆነ የቁጥጥር ስርአት ተዘርግቶ ህዝባዊ የምክክር መድረክ እስኪከናወን ድረስ በአገሪቱ ውስጥ ማንኛውም የዘረመል ልውጥ ህያዋን የማሳ ላይ ሙከራና ለሽያጭ የሚውል የሰብል ምርት በተመለከተ ከአምስት (5) አመት ላላነሰ ግዜ በመንግሰት እግድ እንዲተላለፍበት እንጠይቃለን፡፡
  2. የዘረመል ልውጥ ህያዋን በሚመለከት በግብርና ስርአታችን ውስጥ እናካትተው ወይስ ይቅር በሚል አስቸኳይ ህዝባዊ የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ፡፡
  3. አገራችን የካርታኼና ፕሮቶኮል ለማስፈፀም የገባችውን ቃል እንድታከብር፤ እንዲሁም መንግስት ብዝሃ-ህይወቱን እና የሰዎች ጤንነትን ለማስጠበቅ ያወጣቸውን ህጎችና ደምቦች መሬት ላይ እንዲተገብር፡፡
  4. የአገራችን ችግሮችን የመቋቋም፣ የልዩ ማንነታችን እንዲሁም የወደፊት እጣ ፈንታ መሰረት የሆኑን የእፅዋትና የእንስሳት ብዝሃ-ህይወት ሀብት ላይ በዘረመል ልውጥ ህያዋን አቀንቃኞች በኩል የሚሰነዘረው ማጥላለትና የሚደረገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆም፡፡
  5. የማህበረሰብ ጤናና የአካባቢ ደህንነት ለመጠበቅ ተብለው የተደራጁ ተቋማት አቅም በተገቢው መንገድ መገንባትና ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
  6. የዘረመል ልውጥ ምርቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ግልፅና አሳታፊ የሆኑ አሰራሮችን በተግባር እንዲውሉ ይደረግ፡፡
  7. Read also:በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ ላይ የተመዘገበው የባሌ ተራራሮች ብሔራዊ ፖርክ አደጋ ላይ…

ፈራሚዎች፡-

  1. ፔለም ኢትዮጵያ ኮንሶርትየም፡ ኢሜል – hailuara@yahoo.com; ስልክ – +251 911 246046 2. የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበር: ኢሜል – gbdagaga@gmail.com; ስልክ – +251 911 945616
  2. ፔስቲሳይድ አክሽን ኔክሰስ ኢትዮጵያ: ኢሜል – pan.ethiopia@gmail.com; ስልክ – +251 116 186774
  3. የዘላቂ ልማት መካነ ጥናት
  4. መልካ ኢትዮጵያ
  5. ምርጥ ተሞክሮ ማህበር
  6. ፓርትነርሺ ፎር ኦቪሲ ኢትዮጵያ
  7. ቮይስ ኦፍ ዋይልደርነስ ደቨሎፕመንታል ኦርጋናይዜሽን
  8. አሶሳ የአካባቢ ጥበቃ ማህበር

10.መሰረት ሁማኒታሪያን ኦርጋናይዜሽን

11.ሪፍት ቫሊ ኢኒሼቲቭ ፎር ሩራል አድቫንስመንት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe