በኢትዮጵያ 65 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ተመርቀዉ ስራ ለማግኘት አዳጋች እንደሆነባቸው አዲስ ጥናት አመለከተ

በአፍሪካ አመራር ዩኒቨርሲቲ የተደረገው የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ከትምህርት በኋላ ወደ ስራ የሚገቡ ተማሪዎች ሁለት ሶስተኛ (65%) የሚሆኑት ከትምህርታቸው በኋላ ባለው ውስን የስራ ዕድል ላይ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በዘጠኝ የአፍሪካ አገራት ከ8,000 የሚበልጡ ተሳታፊዎችን ያሳተፈው ጥናቱ፣ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ስራ ገበታ ሲገቡ የሚገጥሟቸው ዋና ዋና ስጋቶችን የዘረዘረ ሲሆን የስራ ዕድል እጥረት (65%)፣ ምቹ ያልሆነ የኢኮኖሚ ሁኔታ (37%) እና በቂ የስራ ልምድ አለመኖር (29%) ናቸዉ።
በተጨማሪም 24% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች ከምረቃ በኋላ የስራ ዕድል የማግኘት ችሎታቸው ላይ እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል ብሏል።
የ2025 የአፍሪካ የሰው ኃይል ዝግጁነት ጥናት” የተሰኘው ይህ የመጀመሪያው አህጉራዊ ጥናት፣ ስለ ከፍተኛ ትምህርት፣ ስለሙያ ዕድሎች እና ስለ ኢኮኖሚው የወጣት ተመራቂዎች እና አሰሪዎች አመለካከት ላይ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን እንደሚሰጥ ካፒታል ከሪፖርቱ ለመረዳት ችሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe