በኢትዮጽያ ተጠልለለው የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር 1 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱ ተነገረ

በኢትዮጽያ ተጠልለለው የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር 1 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱ ሲነገር 15 ኢትዮጽያዊን ስደተኞች በኤርትራ ይገኛሉም ተብሏል፡፡

ከ179ሺ በላይ ኤርትራዊያን በኢትዮጽያ ይገኛሉ ሲል ይፋ ያደረገው የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ነው፡፡

163ሺ ኢትዮጽያን ስደተኞችም በተለያዩ ጎረቤት ሀገራት በስደተኝነት ተመዝግበው እንደሚገኙ ገልጻል፡፡

በሱዳን ከ68ሺ በላይ ኢትዮጽያዊያን ይገኛሉ የተባለ ሲሆን፤ከ93ሺ በላይ ሱዳናዊያን ከጦርነት ሸሽተው በኢትዮጽያ ተጠልለው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ወቅት በኢትዮጽያ ከ11 ሀገራት የመጡ ስደተኞች አሉ የተባለ ሲሆን ቁጥራቸውም አንድ ነጥብ አንድ ሚሊየን ነው ብሏል፡፡

ደቡብ ሱዳናዊያን ከ430ሺ በላይ የሚሆነውን ቁጥር በመያዝ ከፍተኛ ናቸው ተብሏል፡፡ በደቡብ ሱዳን ደግሞ ከ7ሺ በላይ ስደተኛ ኢትዮጽያዊያን እንዳሉ ተሰምቷል፡፡

ከ360ሺ በላይ ሶማሊያዊያን በኢትዮጽያ ተጠልለው ይገኛሉ ሲባል በሶማሊያ ደግሞ ከ28ሺ በላይ ኢትዮጽያዊያን ተጠልለው አሉ ተብሏል፡፡

በኬኒያ ከ43ሺ በላይ ኢትዮጽያዊያን ስደተኞች መገኘታቸው ሲገለጽ፤ከ5ሺ በላይ ኬኒያዊያን ደግሞ በኢትዮጽያ በስደተኝነት ተመዝግበው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ገልጻል፡፡ በዩጋንዳም በትክክል ቁጥራቸው ባይታወቅም በ100ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጽያዊያን እንዳሉ ይነገራል፡፡

56 ጂቡቲያውያን በኢትዮጽያ በስደተኝነት መኖራቸውም ታውቋል፡፡ 14ሺ የሚደረሱ ኢትዮጽያዊያን ደግሞ በጅቡቲ በስደተኝነት ይገኛሉ ተብሏል፡፡

749 ሶሪያዊያን ፡133 የብሩንዲ ዜጎች፡27 ሊባኖሳዊያን በኢትዮጽያ እንዳሉም የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ነው የገለጸው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe