“በኢንተርኔት ላይ የተጣለው ዕቀባ መንግስትን እንጂ እኔን አይመለከትም” – የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታም

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተጣለው ዕቀባ መንግስትን እንጂ” እርሳቸው የሚመሩት ተቋምን እንደማይመለከት ተናግረዋል፡፡ፍሬሕይወት ይህን የተናገሩት የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀማቸውን ያቀረቡት ስራ አስፈፃሚዋ ተቋሙ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግና የተጠቃሚን ቁጥር ለመጨመር በተለያዩ የኔት ወርክ ደረጃዎች ወደ ሕዝቡ ለመድረስ መስራቱን አመልክቷል፡፡

በዚህም ከ84 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ማፍራት መቻሉን ገልፀዋል፡፡ የመንግስትና የንግድ ተቋማት የክፍያ ስርዓታቸውን በቴሌ ብር እንዲፈፅሙ በማድረግ 30.5 ሚሊየን ብር በላይ የቴሌ ብር ተጠቃሚዎችን ማፍራት እንደቻሉ የጠቀሱት ፍሬሕይወት በዚህም 394.7 ቢሊየን ብር በላይ በቴሌ ብር ግብይት መፈፀሙን ስራ ተናግረዋል፡፡

ከስራ አስፈፃሚዋ ሪፖርት በኋላም ከቋሚ አባላቱ በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ‹ ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር ምን እየተሰራ ነው› ፤ ” ገደብ የተጣለበት ኢንተርኔት ተቋሙ ለሚያካሄደው ስራዎች እንቅፋት እየሆነ ነው ይህን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው” የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም በጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች የተቋረጠውን የቴሌኮም አገልግሎት መልሶ ለመገንባት ተቋሙ ጥረት እያደረገ መሆኑ የጠቀሱት ስራ አስፈፃሚዋ የተወሰኑ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልፀዋል፡፡በቴሌኮም መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችንና ስርቆቶችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑን ሀላፊዋ ጠቅሰዋል፡፡

“በኢንተርኔት ላይ የተጣለው ገደብ ተቋሙን የሚመለከት ሳይሆን በመንግስት አካል የተጣለ ገደብ ስለሆነ ከሚመለከተው አካል በሚሰጥ ፍቃድ የሚነሳ መሆኑን” ስራ አስፈፃሚዋ አብራርተዋል፡፡የትኛው የመንግስት አካል እንደሆነ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe